The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

News

ለታገዱት አቅራቢዎች ምህረት ተደረገላቸው

የመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ኤጀንሲ ከመንግስት መ/ቤቶች በተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ላይ የቀረቡ የጥፋተኝነት ሪፖርት መነሻ በማድረግ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 እና ለዚሁ አፈጻጸም በወጣው የፌዴራል መንግስት የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ጉዳያቸው ታይቶ በማንኛውም የመንግስት መ/ቤት ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ እየታገዱ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በ2012 በጀት ዓመት በፌዴራል መንግስት መ/ቤቶች ላይ ጥፋት በመፈጸማቸው  ምክንያት ብዛት 58 ያህል አቅራቢዎች የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ  የታገዱ ሲሆን ከእነዚህ አቀራቢዎች ውስጥ ጥፋታቸውን በማመን፣ ነገር ግን አሁን በተፈጠረው ወረርሽኝ ምክንያት ሰራተኛ መቀነስ እንዳይችሉ የህግ ክልከላ የተጣለ በመሆኑና አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው የተቀዛቀዘ በመሆኑ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለጽ ያቀረቡትን የምህረት ጥያቄ መነሻ በማድረግ እና ድርጅቶቹ በመንግስት ጨረታ ላይ ቢሳተፉ ተወዳዳሪነትን በማስፋት መንግስት ከግዥ ማግኘት የሚጠበቅበትን ተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በማስቻል ረገድ የሚኖረውን አዎንታዊ አሰተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ ሚኒስቴር በተጻፈ ደብዳቤ በሙስናና ማጭበርበር ምክንያት ከታገዱት አቅራቢዎች ውጪ እገዳው በምህረት እንዲነሳላቸው ወስኗል፡፡
ስለሆነም ታግደው ከነበሩት 58 አቅራቢዎች ውሰጥ 45 አቅራቢዎች በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ተላልፎ የነበረው እገዳ ተነስቶላቸው ከመስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የመንግስት ግዥ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የመንግስት ግዥ አፈፃፀምና ንብረት ማስወገድ አቤቱታ ማጣራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሱ አብዲ ገልጸዋል፡፡


የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በግዥና ንብረት አሰተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ዙሪያ ሐምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በገንዘብ ሚኒስቴር አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ፡፡

በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የዋና ዳይሬክተር አማካሪ የሆኑት አቶ ነጋሽ ቦንኬ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናውን የሰጡ ሲሆን፣ ስለአዋጁ ማሻሻያ ዋና ዋና ዓላማዎች፣ በአዋጁ የተካተቱት ዋና ዋና የማሻሻያ ለውጦች እና ማሻሻያውን ማድረግ  ያስፈለገባቸው ምክንያቶች እንዲሁም ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር በተያያዙ ስለተካተቱ አሰራሮች ላይ ገለጻ አድርጓል፡፡

በመቀጠልም አማካሪው በአፈጻጸም ሲያጋጥሙ የነበሩ እና   ለመልካም    አስተዳደር   ችግር ምክንያት የሆኑ    የአሰራር ጉድለቶች ስለማረም፣ የመንግስት የልማት  ድርጅቶች የመንግስት ግዥና   ንብረት     አስተዳደር ወጥ በሆነ    መንገድ የሚመራበትን ስልት ስለመቀየስ፣ የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎችን ተሳትፎ የማበረታት ስልት፣ አዋጁን የተሟላ የሚያደርጉ ተጨማሪ ድንጋጌዎችን ስለማካተት የአዋጁን አወቃቀር በማስተካከል ለአፈጸጸም በይበልጥ አመቺ ስለማድረግ፣ በግዥ ሂደት የሚነሱ አቤቱታዎችን ማጣራት እና  ውሳኔ አሰጣጥ    ሂደትን ገለልተኛ እና ተዓማኒነት እንዲኖረው ስለማስቻል፣ እንዲሁም የመንግስት ኤሌክትሮኒክ   ግዢ ሥርዓትን    በአዋጁ በማካተት ዘመናዊ የንብረት    አስተዳደር  ሥርዓትን እንዲኖር ማድረግ በሚል በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡በመጨረሻም አቶ ወልደአብ ደምሴ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በማጠቃለያው ንግግር ላይ እንደተናገሩት ግዥ ማሳለጫ እንጂ ማደናቀፊያ መሆን እንደሌለበት፣ ግዥን ዘመናዊ በማድረግ የስጋት ተጋላጭነትን መቀነስ፣ በCheck and Balance አመኔታን ማሳደግ እና የሰው ንኪኪን በመቀነስ ግልጽነት ያለው አሰራር መስራት መሆኑን ገልጸው፣ የመንግስት አጠቃላይ ዓላማው ሕዝቡ ግዥ ላይ አመኔታን እንዲያገኝ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለግማሽ ቀን በቆየው በመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ዙሪያ ውይይት ላይ የሚመለከታቸው የመንግስት የልማት ድርጅቶች የበላይ ሃላፊዎችና የግዥ ስራ ክፍል ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

eGP

ለመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳዳር ኤጀንሲ የውጪ ተገልጋዮች

የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ተሰጠ

የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለስድስተኛ ጊዜ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ ተሰጠ
የመንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2009 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ደረጃ መስጠት የተጀመረውን የግዥና የንብረት አስተዳደር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለስድሰተኛው ዙር ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዩንቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ከታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም.  እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ሥልጠና ሰጠ፡

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 ዓ.ም. ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከሚያከናውናቸውም ዋና ዋና ተግባራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የግዥና የንብረት አስተዳደር ሥርዓቱ ወጥነት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ የሆነና ግልጽነት የተላበሰ የሙያ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመራ ማስቻል ነው፡፡


ከፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር የተሰጠው ስልጠና በBasic level, Essential level and Advanced level በሚል በሶስት ደረጃ የተከፋፈለ ሆኖ ስለግዥ አዋጅ፣ መመሪያ፣ ማኑዋል፣ ስለጨረታ ሰነድ እንዲሁም ስለዓለም ዓቀፍ ግዥ ምርጥ ተሞክሮ፣ ስለግዥ ዘዴዎች፣ ስለግዥ ዕቅድ፣ ሰለ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና እርምጃዎች፣ ስለንብረት አያያዝና አጠቃቀም እንድሁም አወጋገድን በሚመለከት ሰፋ ያለ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ይህ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ቀጣይነት ያለው ሲሆን፣ በዘርፉ የሚታዩትንም የአቅም ክፍተቶች ዘላቂነት ባለው መልኩ ይፈታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ሰልጣኞችም በቡድን ስራ የተሳተፉ ሲሆን፣ በመጨረሻም የመመዘኛ ፈተና በመስጠት ሶስቱም ደረጃ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሥልጠናው ተጠናቋል፡፡
በመሆኑም 70 ከሚሆኑ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ የግዥና የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች በBasic level, Essential level & advanced level በድምሩ ለ190 ሠልጣኞች ሥልጠናው ተሰጥቷል፡፡

More Articles...