The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

News

ኤጀንሲው በአማካሪ ባስጠናው መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

በፌደራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለክልሎችና ለከተማ መስተዳድሮች በአማካሪ ባስጠናው SIMPLIFIED WEREDA SYSTEM የግዥ አገልግሎት መመሪያ የመጀመሪያ ረቂቅ ዙሪያ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከመጋቢት 28–29 ቀን 2007 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
አቶ ጆንሴ ገደፋ የመንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ—ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የዉይይት መድረኩ ዋና ዓላማ ለሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች SIMPLIFIED WEREDA SYSTEM የግዥ አገልግሎት መመሪያ በመጀመሪያ ረቂቅ ዙሪያ የግንዛቤ መስጨበጫ ሥልጠና ለመስጠትና የማሻሻያ ግብዓቶችን ከተሳታፊዎች ለማሰባሰብ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
በመቀጠልም ም/ዋና ዳይሬክተሩ ሁሉም ወረዳዎች ሊጠቀሙበት የሚችሉ አንድ ወጥ የሆነ ቀለል ያለ የወረዳዎችን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የግዥ አገልግሎት መመሪያ ለማዘጋጀት እንደሆነ ጠቁመው፤በናሙና ዳሰሳ ጥናቱም የተለያዩ ያጋጠሙና ሊያገጥሙ የሚችሉ ችግሮች ምን እንደሆነ? በእነዚህና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ያለንን አስተያየት መስጠት፤ ጥያቄ በመጠየቅ፣  ሥራ ላይ በምናውልበት ጊዜ ሊያጋጥሙን የሚችሉ ስጋቶችን ማንሳት እንዳለባቸው በመግለፅ ለዕለቱ የቀረበውን የዳሰሳ ጥናት ዉይይት አስጀምረዋል፡፡
የላይፍ አማካሪ ድርጅት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዳምጠው ወልዴ የዳሰሳ ጥናቱ በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳደሮችን በማከለ 53 በሚሆኑ የናሙና ወረዳዎች በመውሰድ የተጠና SIMPLIFIED WEREDA SYSTEM የግዥ አገልግሎት መመሪያ መሆኑን ጠቅሰው፣ የቀረበው ጥናት የመጨረሻና ያለቀለት አለመሆኑንና ከተሳታፊዎች ብዙ ግብዓት እንደሚገኝ በመጥቀስ ወደ ገለፃ ግብተዋል፡፡
ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች የተውጣጡ የግዥና ንብረት አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የቀረበው ቀለል ያለ የግዥ አገልግሎት መመሪያ አግባብ መሆኑን ጠቅሰው ለወረዳዎች በሚያመች መልኩ መዘጋጀቱ ብዙ የወረዳዎችን ችግር እንደሚቀርፍ ይታመንበታል በማለት ገልፀዋል፡፡

በመቀጠልም ቀለል ያለ የግዥ አገልግሎት መመሪያ ዙሪያ በተዘጋጀው ዉይይት መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ የማሻሸያ ግብዓቶችን በማንሳት፣ግልፅ ያልሆነላቸውን ጥያቄ በመጠየቅና አስተያየቶችን በመስጠት ተሳትፈዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በቆየው የፌደራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአማካሪ ባስጠናው SIMPLIFIED WEREDA SYSTEM የግዥ አገልግሎት መመሪያ የመጀመሪያ ረቂቅ ዉይይት መድረክ ላይ ከ100 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

የፌደራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለመላው ኤጀንሲው ሠራተኞች በሙስና ወንጀል ጥቆማ አቀባበል፤ የአያያዝ ሥርዓትና የማጣራት ስራን በተመለከተ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ፡፡
የስብሰባው አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ መንገሻ በመንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የሥነ—ምግባር ከፍተኛ ባለሙያ በመግቢያው ላይ እንደተናገሩት  የሥልጠናው ዓላማ ሙስናንና ሥነ-ምግባርን በሚመለከት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሲሆን፤ በአገራችን ግዥ ከፍተኛውን የመንግሥት በጀት ስለሚይዝና ውስብስብም በመሆኑ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው፡፡ ለዚህም በአዋጅ ቁጥር 649/2001 ሥልጣን በተሰጠው መሠረት የመንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የግዥ አሰራርን ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን፤ ለቁጥጥርም እንዲያመች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በመስጠት የሚተጋ ተቋም መሆኑን ገልጸው ተሳታፊዎች በጥሞና እንዲከታተሉ በማሳሰብ  ስልጠናውን አስጀምረዋል፡፡
አቶ ደረጀ ምትኬ በፌዴራል የሥነ—ምግባርና ፀረ—ሙስና ኮሚሽን ከፍተኛ የችሎት ዐቃቤ ህግ ሥልጠናውን  የሰጡ ሲሆን፤ በሥልጠናውም ሙስና የአንድ አገርን ዕድገት የሚያቀጭጭ፤ ለመልካም አስተዳደር እንቅፋት የሚሆን ይልቁንም ዜጎች በየተቋማቱ ሊያገኟቸው የሚገቡ የመንግስት አገልግሎቶች በሙስና ሊጎተትና ሊለወጥ የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ዕውን መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በመቀጠልም ስለ ፌደራል የሥነ—ምግባርና ፀረ—ሙስና ኮሚሽን መሠረታዊ ዓላማዎች፤ ኮሚሽኑ ጥቆማ የሚቀበልበት የህግ ማዕቀፍና  በሥልጣን ክልሉ የሚወድቁ ጉዳዮች፤ ኮሚሽኑ ጥቆማ የሚቀበልበት ሥርዓት፤ ለኮሚሽኑ የቀረበው ጥቆማ   ስለሚጠናቀርበትና ለውሳኔ ስለሚቀርብበት ሁኔታ፤ የመረጃ ገምጋሚና ወሳኝ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር፤ ለኮሚሽኑ የቀረበው ጥቆማ ስለሚያዝበት ሥርዓት፤ የጠቋሚዎች መብት:-የተወሰነን ውሳኔ የመጠየቅ መብትና ቅሬታ የማቅረብ መብት፤ከኃላፊነት ነፃ ስለመሆንና የጠቋሚዎች ጥበቃ ምን ይመስላል? በሚል ገለፃ አድርገዋል፡፡

Read more...

በመንግሥት ግዥ አፈጻጸም ዙሪያ ለፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ሥልጠና ተሰጠ

በፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በግዥ አፈጻጸም ዙሪያ ከሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ ሰልጣኞች ከየካቲት 2 እስከ የካቲት 6/2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለአምስት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
የሥልጠናው ዓላማም በዋናነት በፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች በግዥ አፈጻጸም ሥርዓትና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍና እንዲሁም ግዥ ከፍተኛውን የመንግሥት በጀት ስለሚይዝ ጥንቃቄ አንደሚያስፈልገውና የተሻለ የግዥ ሥርዓት ለማስፈን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Read more...

በመንግስት ንብረት አስተዳደር ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ

የፌደራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግስት ቋሚ ንብረት አስተዳደር  እና በስቶክ አስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ሥልጠና ለሚመለከታቸው የፌደራል ባለበጀት መ/ቤቶች የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከየካቲት 9-13 ቀን 2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ሰጠ፡፡
የፌደራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደበበ ማሞ እና የጥናትና መረጃ ትንተና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ደምሱ አብዲ፣እና የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች ደረጀ ኃ/ማሪያም እና ወ/ሮ አያልነሽ ዓለሙ ሥልጠናውን የሰጡ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማ ውጤታማና ዘመነዘዊ የስቶክ አስተዳደር መርህንና ሥርዓትን እንዲረዱ፣የስቶክ አስተዳደር ተግባራትን የማከናወን አቅም ለማዳበር በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የንብረት አስተዳደር እና የስቶክ አስተዳደር ህግጋትንና ሥርዓትን ጠንቅቀው እንዲያወቁ ግንዛቤ ለመስጠት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
አሰልጣኞቹ አጠቃላይ ስያሜን፣ስቶክ መለየትና መመደብን፣መቀበል እና መፈተሽን፣ወጪ ማድረግን ፣የስቶክ መዛግብት የሂሳብ ሥርዓትና ሪፖርትን፣ስቶክ ቆጠራና ቁጥጥርን፣ክምችትን፣ መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቦችና መርሆዎችን፣በመንግስት ይዞታ ስር የሚገኙ ቋሚ ንብረቶች የአስተዳደር መዋቅር፣የመጀመሪያ አጠቃላይ ቆጠራ እንቅስቃሴና የመዝገብ ዝግጅት ሂደት ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም ስለቋሚ ንብረት አወጋገድ፣ሪፖርት ስለማቅረብ፣ለቋሚ ንብረት ዋጋ ስለመመደብ፣የቋሚ ንብረቶች መዛግብት አያያዝ ሂደት፣የቋሚ ንብረቶች ዋጋ በሂሳብ እንዴት እንደሚያዝ፣የቋሚ ንብረቶች የዕርጅና ቅናሽ፣ሌሎች ጉዳዮች እና የአቤቱታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በሚሉ ርዕሶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

Read more...

የ2007 የመጀመሪያው የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸምን በሚመለከት ውይይት ተደረገ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለመላው የኤጀንሲው ሠራተኞች የ2007 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ታህሣሥ 29 ቀን 2007 ዓ.ም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡

አቶ ጆንሴ ገደፋ የፌደራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ በኤጀንሲው ያሉት ዳይሬክቶሬቶች  ከመልካም አስተዳደር፣ ከለውጥ ሰራዊት እና ከሕዝብ ክንፍ ውይይት አንፃር  ያለፈው 6 ወራት  የዕቅድ አፈጻጸም ሥራ ምን ይመስላል? በሚለው ላይ ለመወያየት መሆኑንና የውይይቱም ተሳታፊዎች ጥያቄ በመጠየቅና አስተያየት በመስጠት በንቃት መከታተልና መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመቀጠልም አቶ አድማሱ ማሞ የለውጥ ትግበራ ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከተገልጋይ፣ ከፋይናንስ፣ ከውስጥ አሠራር፣ ከመማማርና ዕድገት እይታዎች አንጻር በየዳይሬክቶሬቱ በ2007 በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የታቀዱ የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች ላይ ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ፋይናንስን በሚመለከት ኤጀንሲው የተመደበለትን በጀት የተገልጋዮችን አቅም ለማገልበትና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት በጀቱን በቁጠባና በአግባቡ በስራ ላይ ለማዋል ትኩረት የሚሰጠው l መሆኑን እና የውስጥ አሠራርን  ደግሞ የግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓቱን በማጣጣም ተቀባይነቱን የማሳደግ፣የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን የማሻሻል፣አቤቱታ የማጣራትና ውሳኔ አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ  መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም የኤጀንሲውን የሥርዓተ—ጾታ ሥራ መሠራቱን እና የ1 ለ5 አደረጃጀት ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው ዋናው ነገር ተገልጋዮችን ማርካት መሆኑንና ስለአጋጠሙም ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች በማንሳት አስረድተዋል፡፡
በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በቆየው የኤጀንሲው የ2ዐዐ7 የመጀመሪያው የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ውይይት ላይ ከ70 በላይ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

More Articles...