The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

News

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት እና ከኦዲት ቦርድ ሠራተኞች ጋር በመሆን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የፀረ-ሙስናን ቀን ህዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒሰቴር የስብሰባ አዳራሽ አከበረ፡፡

አቶ ይልማ ዘውዴ በገንዘብ ሚኒሰቴር የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በህልውናችን ላይ የተጋረጠውን ሙስናን በመግታት እድገታችንን  ለማፋጠን እንረባረብ የሚለውን በንባብ ካሰሙ በኋላ፣ ስለሙስና ትርጉምና መገለጫዎቹ፤ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ስለሚዳርጉ መንስኤዎች፤ የሙስና ዓለም አቀፍዊ  ሁኔታው  በኢትዮጵያ ላይ ስለአሳረፈው ተጽዕኖ፤ ስለሀገራዊ የፀረ ሙስና ትግሉ እንቅስቃሴና የተገኘ ውጤት፣ስለስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ትግሉ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ በዝርዝር አሰረድተዋል፡፡

ወ/ሮ ከበቡሽ ሽፈራው በፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ አገልግሎት የስነምግባርና የፀረ- ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባቀረቡት ጽሁፍ ከሙስና ወንጀል ሕጎች ተነስተው ስለወንጀል ምንነት፣ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት መሟላት ስላለባቸው ሁኔታዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች በመንግሥት ሥራ ላይ ሰለሚፈፅሟቸው ወንጀሎች፣ ሌሎች ሰዎች በመንግሥት ሥራ ላይ ሰለሚፈፅሟቸው ወንጀሎች፣ ሰለዝርዝር የሙስና ወንጀል ድንጋጌዎች፣ በሥልጣን አለአግባብ ስለመገልገል፣  የማይገባ ጥቅም ሰለመቀበል፣ የመንግሥት ሥራን በማያመች አኳኋን ስለመምራት፣ በሥልጣን ሰለመነገድ፣ ያለአግባብ ጉዳይን ሰለማጓተት፣ ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ሰለማግኘት፣በሌለው ሥልጣን ስለመጠቀም ሰፋ ባለ መልኩ አሰረድተዋል፡፡ በመጨረሻም ከፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በሁለት የኤጀንሲው ሰራተኞች ስለ ሙስና ግጥሞች የተነበቡ ሲሆን ለበዓሉም ድምቀትን ሰጥቶታል፡፡ በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸው የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡
ለግማሽ ቀን በቆየው የፀረ-ሙስና ቀን በዓል አከባበር ላይ የገንዘብ ሚኒሰቴር እና የተጠሪ መ/ቤቶች ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ.የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ለተመረጡ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች በመንግስት ግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለተመረጡ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች በመንግስት ግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ዙሪያ ከጥቅምት 6 እስከ ህዳር 30/2012 ዓ.ም. የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

አቶ ነጋሽ ቦንኬ  የክብርት ዋና ዳይሬክተሯ አማካሪ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና ዓላማ የፋይናንስ ዘርፍ የሆነውን የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም የግዥ ሂደት እና የንብረት አወጋገድ ተግባራት ለዚህ ዓላማ የተዘጋጁ የህግ ማዕቀፎችን በጠበቀ መልኩ ማስኬድ እንዲቻል፣ ይልቁንም የፌድራል ባለበጀት መ/ቤቶችን የመፈጸም አቅም በማሳደግ፣ በዕቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም፣ የበጀት አፈጻጸማቸውንና የግዥ አፈጸጸም ግንዛቤን በማሳደግ ለሚሰጡት አሰተዳደራዊ ውሳኔ ተጠያቂነት እንዲያጎለብቱ የሚያደርግ የአሰራር ሰርዓትን በማስረጽ የህግ የበላይነትን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ የታለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ለተመረጡ የፌዴራል ባለበጀት ተቋማት በተዘጋጀ የግዥ አፈፃፀም እና የንብረት አስተዳደር የአቅም ማሳደጊያ ስልጠና ላይ የተለያዩ አሰልጣኞች ሥልጠና የሰጡ ሲሆን፣ ስለመንግስት ግዥ አጠቃላይ ገጽታ፣ የመንግስት ግዥ ስለሚመራባቸው የህግ ማዕቀፎች፣ ስለመንግስት ግዥ ዓላማና መርሆች፣ በመንግስት ግዥ አፈጻጸም ሊኖር ስለሚገባ ተግባር እና ኃላፊነት፣ ስለግዥ አፈጻጸም ሂደት እና ስለውል አስተዳደር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመቀጠልም አሰልጣኞቹ ስለመንግስት ግዥና ንብረት አወጋገድ አቤቱታና የጥፋተኝነት ማጣራት ሂደት አጠቃላይ ገጽታ፣ በአፈጸጸም ስለታዩ የአሰራር ችግሮች፣ ስለአቤቱታ የአቀራረብ ሥነ-ሥርዓት፣ ሰለ ግዥ አፈጻጸምና ንብረት አቤቱታ አጣሪና ውሳኔ ሰጪ ቦርድ እንዲሁም ስለመንግስት ተሸከርካሪዎቸ ስምሪትና ነዳጅ አጠቃቀም እና ስለመንግስት ንብረት አወጋገድ ሂደት፣ ስለ ግዥና ንብረት ኦዲት ሂደቶች የኦዲት ሪፖርቱ ስለሚይዛቸው ዋና ዋና ይዘቶች ስለ መንግስት ግዥና ንበረት ኦዲት እና ክትትል የ2011 ዓ.ም ዕቅድና ክንውን እና በ2011 በጀት ዓመት በኦዲት ወቅት የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶች ላይ አጠቃላይ ገለጻ አድርጓል፡፡

በሥልጠናው ላይ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቂ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
ለአንድ ወር ውሰጥ በአራት ጊዜ ተከፋፍሎ  ለተመረጡ ተቋማት በተሰጠው ሥልጠና ላይ 500 የሚሆኑ በቀጥታ ለሚመለከታቸው ለየተቋማቱ የሥራ ሃላፊዎች፣ የአሰተዳደርና ፋይናንሰ ዳይሬክተር፣ የግዥ ዳይሬክተር፣ የንብረት ዳይሬክተር፣ የግዥ አጽዳቂ ኮሚቴ አባላትና የውስጥ ኦዲት አገልግሎት ዳይሬክተር ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ኤጀንሲው E-GPን በሚመለከት የግምገማዊ ዓወደ-ጥናት አካሄደ

የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚተገበረው የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (Electronic Government Procurement)ን የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡በመሆኑም PERAGO Information System ያዘጋጀውን የE-GP Business Process Reviewን በሚመለከት ለሙከራ ከተመረጡ መ/ቤቶች ጋር ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒሰቴር አዳራሽ የግምገማዊ ዓውደ ጥናት አካሄደ፡፡

በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የዋና ዳይሬክተር አማካሪ የሆኑት አቶ ነጋሽ ቦንኬ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (Electronic Government Procurement) በማስተዋወቅ ሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመው፣ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ማለት ተጠቃሚዎች በInformation Technology በመታገዝ ግዥን ከመደበኛ የግዥ ሂደት ወደ ኤሌክትሮኒክ የግዥ ሂደት በመውሰድ መቆጣጠር እንዲችሉ የማድረግ የግዥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም አቶ ነጋሽ ቦንኬ ብዙ የአፍሪካ አገሮች እና በዓለም ላይ ያሉ አገሮች የግዥሥርዓታቸውን ለማሻሻል E-GPን በማሰሪያነት እየተጠቀሙ መሆናቸውን ገልጸው፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲም ከ2010ዓ.ም ጀምሮ ብዙ ስራዎችን በመስራት የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን በማረገገጥ ላይ መሆኑን አሰረድተዋል፡፡

አማካሪው አቶ ነጋሽ ቦንኬ የዛሬው ዓወደ ጥናት PERAGO Information System ባጠናው Business Process Review የመጀመሪያው ረቂቅ ላይ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ አማካሪ ድርጅት የE-GP Information System ለሙከራ በተመረጡ መ/ቤቶች በስራ ላይ ስላጋጠመው ችግሮች እና ሰለሚጠበቁ ሥርዓቶች ለማስረዳት መሆኑን ገልጠዋል፡፡
በሥልጠናው ላይ ለሙከራ ከተመረጡ መ/ቤቶች የተለያዩ ዶክመንቶች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን፣ በወይይቱም ላይ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቂ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
ለአንድ ቀን በቆየው E-GP Business Process Reviewን ዓውደ ጥናት ሰነድ ላይ ኤጀንሲው ሥራ አመራሮች፣ባለሙያዎች እና ለሙከራ ከተመረጡ የፌዴራል መ/ቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ኤጀንሲው የተቆጣጣሪነት ሚና ላላቸው ፌዴራል ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር የተቆጣጣሪነት ሚና ላላቸው ለስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣ ለዳኞች እና ለጠቅላይ አቃቢ ህግ እንድሁም ከተመረጡ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ከነሐሴ 09 አስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ኩሪፍቱ ሪዞርትና ሆቴል መሰብሰቢያ አደራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ወ/ሮ መቅደስ ብርሃኑ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት በመክፈቻው ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ዋና ዓላማ የመንግስት ፋይናንስ ዘርፍ የሆነውን የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም የግዥ ሂደት ተግባራት አግባብ ባለው መልኩ ማስኬድ እንዲቻል የተቆጣጣሪነት ሚና ላላቸው ባለድርሻ አካላት በተቆጣጣሪነት ሙያ ላይ ለተሰማሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት በግዥ ላይ የሚውለው ከፍተኛ የሀገሪቷ ሀብት አግባብ ባለው መልኩ በስራ ላይ እንዲውል ለማስቻል ሀገራዊ ሀላፊነታችንን በተገቢው መልኩ ለመወጣት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተውጣጡ አሰልጣኞች በመንግስት ግዥ አላማና መርሆዎች፣ የመንግስት ግዥ የሚመራባቸው ሰነዶች፣ የግዥ ዕቅድና የግዥ ዑደት፣ በመንግስት ግዥ የሚታዩ ክፍተቶች፣ በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ዙሪያ የሚታዩ ስነ-ምግባር ጉድለት እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ጥሩ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የተቆጣጣሪነት ሚና ካላቸው የፌዴራል ተቋማት ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኤጀንሲው አሰልጣኞችና አመራሮች መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡በአዳማ ከተማ ኩሪፍቱ ሪዞርትና ሆቴል ለሶስት ቀናት በቆየው በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ላይ በርካታ የተቆጣጣሪነት ሚና ያላቸው የፌዴራል ተቋማት ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ከኤጀንሲው ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

የፌዴራልመንግሥት የግዥና የንብረትአስተዳደርኤጀንሲለመላውየኤጀንሲውየበላይ ኃላፊዎች እና ሠራተኞችየ2011 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀምን እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድን በተመለከተ ነሐሴ 8 ቀን 2011ዓ.ም. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡ክብርት ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ የመንግስትየግዥናየንብረትአስተዳደርኤጀንሲዋናዳይሬክተርየውይይቱ ዋና ዓላማ የ2011 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀምን እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድን በተመለከተ፣ የ12 ወራት ዕቅድ አፈጻጸማችን ምን እንደሚመስል እና በቀጣዩየበጀት ዕቅድ ዓመት ለምንሰራው ስራ አቅጣጫ መያዝ እንዳለብንለውይይቱ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡አቶ አሰድ አብደላ የዕቅድ ዝግጅትና ክትትልዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር የ2011 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በሚመለከትየ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ለማዘጋጀት መነሻ ይሆን ዘንድ በ2010 አፈፃፀም የነበሩ ጥንካሬዎችንና እጥረቶችን በዝርዝር በመገምገም ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮችን ለይቶ በመውሰድ እንዲሁም በኤጀንሲው ልዩ ትኩረት የሚሹ የስጋት ተጋላጭነት አካባቢዎች መለየት የዕቅድ መነሻ ተደርጎ መወሰዱን፣ዕቅዱ ከተዘጋጀ በኋላ በማኔጅመንትእና በሠራተኞች በየደረጃው በማወያየት ዕቅዱን የማዳበር እና የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጠር ጥረት መደረጉን፣ ከአራቱም ዕይታዎች /ከተገልጋይ፣ ከውሰጥ አሰራር፣ ከፋይናንስ እና ከመማርና ዕድገት/አንጻር እንዲሁም ሰለዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም፣ ስለግብ ተኮር ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም፣ ሰለተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች፣ ሰለክትትልናየግምገማ አፈፃፀም፣ ሰለጋጠሙችግሮች፣ ሰለመፍትሄ እርምጃዎች እና ሰለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሰፋ ያለገለጻ አድርገዋል፡፡በመቀጠልም የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድን በተመለከተ ሰለኤጀንሲው ዕቅድ ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት የ2012 በጀት ዓመት የተከለሰ የኤጀንሲውን ዕቅድን ማዘጋጀት፣ የ2012 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት የሥራ መርሃ-ግብር እና ዓመታዊ፣እና ወርሃዊ የጥሬ ገንዘብዕቅድ ማዘጋጀት፣ የ2012 በጀት ዓመት የግዥ ዕቅድ ማዘጋጀት እና የ2011 በጀት ዓመት የግዥ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣በ2011 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሂደት ወቅት ከታዩ ክፍተቶች በመነሳት የአቅም ግንባታ ሥራ ለመስራት የሚያስችል ዳሰሳ ጥናት ማድረግ፤ በጥናቱ መሠረት ለ2012 በጀት ዓመት የአቅም ግንባታ ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀት እና ለበጀት ዓመቱ ለሥራ ማስፈጸሚያነት የሚውሉ ግብዓቶችን ማሟላት እንደሆነ አሰረድተዋል፡፡በመጨረሻም ክብርትወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ የ2011 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ መቅረቡን ገልጸው፣ የኤጀንሲው ማኔጅመንትም ሪፖርቱን በዝርዝር አይቶ መቅረቡንና ምን ችግር አለ? እንዴትስ እንፍታው? የሚለው ታይቶ ለ2012 የበጀት ዓመት ዕቅድ መነሻተደርጎ መወሰዱን፣ በሪፎርም ሥራዎችም እና በአገልግሎት አሰጣጥም መገምገሙን እና በአጠቃላይ ሪፖርቱ በአብዛኛው በጥንካሬ መገምገሙን ገልጸዋል፡፡በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ከሰራተኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ለግማሽ ቀንበቆየውየኤጀንሲውየ2011በጀትዓመት ዕቅድአፈጻጸም ግምገማ ሪፖርትእና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይትላይ የኤጀንሲው የበላይ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡   

ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

More Articles...