The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

በአቅራቢነት በቀላሉ ለመመዝገብ የሚረዳ የአጠቃቀም ማኑዋል

  1. በገፁ ላይ በስተግራ በኩል “New Supplier Registration” የሚለውን ይምረጡ፡፡

2. “Supplier Registration”የሚለውን ፎርም እንደሚከተለው ይሙሉ፡-

የ ድርጅት ስም ሲያስገቡ ልዩ ምልክት(/.፣,) አይጠቀሙ፡፡

3.ፎርሙን ሞልተው ከጨረሱ በኋላ Register ይበሉት፡፡ ፎርሙን በትክክል ከሞሉ

የሚከተለውን መልዕክት ይመልስልዎታል፡-

4.ፎርሙ ላይ የሞሉትን የኢሜይል አድራሻ (e-mail) ይክፈቱና በተላከልዎት መልዕክት ላይ

የሚጠየቁትን ይፈፅሙ (Activate ያድርጉ) ፡፡

አንድ  Email address ለአንድ  TIN Number  ምዝገባ ብቻ ነው የሚያገለግለው፡፡

በ email አድራሻ የሚላከው activation link በ email inbox ውስጥ ብቻ ሳይሆን በ spam Message ላይ check ያድርጉ፡፡

5.በሲስተሙ ላይ ለእርሰዎ ወደ ተከፈተዉ አካዉንት ለመግባት Home page  ላይ “Members Login” በሚለዉ ላይ
User Name(TIN Number) እና Password የሚሉትን ከሞሉ በኋላ በምስሉ ላይ በቀይ ቀስት የተመለከተዉን
Login የሚለዉን  ይጫኑ፡፡


6.“Login” አድርገው ከገቡ በኋላ የሚከተለውን ገፅ ያገኛሉ፡-

7.“New”  click  ሲያደርጉ የሚቀጥለው ፎርም ይመጣል ፎርሙን ይሙሉ፡፡

8. ፎርሙን ሞልተው ሲጨርሱ “Save” የሚለውን ይጫኑት፣ ከዚያም “Logout” አድርገው ይውጡ፡

ከላይ ያለው ፎርም ሞልተው ከጨረሱ በኃላ የተሳሳቱት መረጃ ካለ የሞሉትን በመምረጥ ‘Detail’ የሚለውን

በመጫን ማስተካከል እና ‘update’ በማድረግ ማስተካከል ይቻላል፡፡

እንዲሁም የስም እና አድራሻ ለውጥ ካለ  ‘profile’ የሚለው ላይ ማስተካል እና ‘update’ ማድረግ፡፡

9.በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ በትክክል ስለመመዝገብዎ ለማረጋገጥ “Suppliers List” የሚለውን ከሜኑ ላይ
ይምረጡና ከሚመጣው ዝርዝር ውስጥ የራስዎን ለማግኘት በ “Tin” ቁጥርዎ አስገብተው ይፈልጉ፡፡
ካገኙት ከ “Tin” ቁጥርዎ ትይዩ ያለችው ሳጥን ላይ ምልክት አድርገው “Detail” የሚለውን በመጫን የሞሉትን
ዝርዝር መረጃ መመልከት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡

በሲሰተሙ ላይ በአቅራቢነት ተመዝግበው ካጠናቀቁ በኋላ የሚሰጥ ሰርተፊኬት/የምስክር ወረቀት የለም፡፡
አጫራች መ/ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡ ድርጅቶችን የሚለዩት በቀጥታ ሲስተሙ ላይ የተመዘገቡ
መሆናቸውን በማረጋገጥ እንጂ ሰርተፊኬት/የምስክር ወረቀት በመመልከት አይደለም፡፡