The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ብሔራዊ የባንዲራ ቀን ተከበረ

 

መንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ

ብሔራዊ የባንዲራ ቀን ተከበረ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርና ከመንግሥት የግዥና የንብረት ማስወገድ አግልግሎት ጋር በመተባበር በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በታችው ግቢ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በድምቀት አከበረ፡፡

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አበበ ሶስቱንም መ/ቤቶች በመወከል በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ፡ — "እኛ ኢትዮጰያውያን፣ የድህነትና ኋላ ቀርነት ዘመን ከአገራንችን ተወግዶ፣ ኢትዮጵያችን በልማትና በዲሞክራሲ ጐዳና በፍጥነት ተራምዳ፣ ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነውን የኢትዮጵያ ህዳሴ ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ እናደርሳለን! የቀሪውን የአንድ ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን ከመንግሥታችን ጐን ተሰልፈን ለማሳካት በሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል እንገባለን፡፡" የሚለውን ቃለ መሃላ በዓሉን ለማክበር ለተሰበሰቡት የሶስቱም መ/ቤት ሠራተኞች አስነብበዋል፡፡

በዚህ ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም በተከበረው የብሔራዊ የባንዲራ ቀን በዓልን ከላይ የተጠቀሱት የሶስቱ መ/ቤት ሠራተኞች በድምቀት አክብረዋል፡፡

 

ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት