The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለመጀመሪያ ጊዜ የንብረት ርክክብ ሥነ-ሥርዓት አካሄደ

ክቡር አቶ ሃጂ ኢብሳ የመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት የመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ታሪኩ ቴፎ ጋር በስጦታ በማስተላለፍ የንብረት ርክክብ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት  በጽ/ቤታቸው ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. አካሂደዋል፡፡

 

በመቀጠልም ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ኤጀንሲው ከሚያዝያ 4-8 ቀን 2013 ዓ.ም በካሄደውን አገራዊ የንብረት ምዝገባ ጊዜ ከተመዘገቡ ንብረቶች ኤጀንሲው ወደ 44,000 ሺህ የሚጠጉ  ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ፋይል ካቢኔት እና የመሳሰሉትን ንብረቶች ከመሸጥ ይልቅ በስጦታ ለሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት መተላለፉ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

አቶ ታሪኩ ቴፎ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ለክልሉ በሥልጠና እደገፈ ያለ መሆኑንና አሁንም ደግሞ በቁሳቁስ በመደገፉ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡