The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው

ከሚያዚያ 4 እሰከ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ያለ አገልግሎት ተከማችተው የሚገኙ የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳር ኤጀንሲ ተገልጿል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ንቅናቄ ዙሪያ የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ ውይይት ተደርጓል፡፡ በቀጣይም ንብረቶቹ ከተመዘገቡ በኋላ ለተጠቃሚ አካላት በማስተላለፍ እና በሽያጭ በማስወገድ ላይ መንግስት በአትኩሮት እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓለማ ሊውል፤ ሲወገድም ለመንግስት ጥቅም ሊያስገኝ በሚያስችል መልኩ ሊወገድና ተቋማት በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ሊተገበር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በገንዘብ ሚኒስቴር የተካሄደው ውይይት ዓላማ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በመለየት፣ የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማመንጨት እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ጭምር ያለመ ነው፡፡

 

የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት