The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ለታገዱት አቅራቢዎች ምህረት ተደረገላቸው

የመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ኤጀንሲ ከመንግስት መ/ቤቶች በተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ላይ የቀረቡ የጥፋተኝነት ሪፖርት መነሻ በማድረግ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 እና ለዚሁ አፈጻጸም በወጣው የፌዴራል መንግስት የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ጉዳያቸው ታይቶ በማንኛውም የመንግስት መ/ቤት ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ እየታገዱ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በ2012 በጀት ዓመት በፌዴራል መንግስት መ/ቤቶች ላይ ጥፋት በመፈጸማቸው  ምክንያት ብዛት 58 ያህል አቅራቢዎች የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ  የታገዱ ሲሆን ከእነዚህ አቀራቢዎች ውስጥ ጥፋታቸውን በማመን፣ ነገር ግን አሁን በተፈጠረው ወረርሽኝ ምክንያት ሰራተኛ መቀነስ እንዳይችሉ የህግ ክልከላ የተጣለ በመሆኑና አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው የተቀዛቀዘ በመሆኑ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለጽ ያቀረቡትን የምህረት ጥያቄ መነሻ በማድረግ እና ድርጅቶቹ በመንግስት ጨረታ ላይ ቢሳተፉ ተወዳዳሪነትን በማስፋት መንግስት ከግዥ ማግኘት የሚጠበቅበትን ተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በማስቻል ረገድ የሚኖረውን አዎንታዊ አሰተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ ሚኒስቴር በተጻፈ ደብዳቤ በሙስናና ማጭበርበር ምክንያት ከታገዱት አቅራቢዎች ውጪ እገዳው በምህረት እንዲነሳላቸው ወስኗል፡፡
ስለሆነም ታግደው ከነበሩት 58 አቅራቢዎች ውሰጥ 45 አቅራቢዎች በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ተላልፎ የነበረው እገዳ ተነስቶላቸው ከመስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የመንግስት ግዥ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የመንግስት ግዥ አፈፃፀምና ንብረት ማስወገድ አቤቱታ ማጣራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሱ አብዲ ገልጸዋል፡፡


የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት