The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ኤጀንሲው E-GPን በሚመለከት የግምገማዊ ዓወደ-ጥናት አካሄደ

የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚተገበረው የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (Electronic Government Procurement)ን የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡በመሆኑም PERAGO Information System ያዘጋጀውን የE-GP Business Process Reviewን በሚመለከት ለሙከራ ከተመረጡ መ/ቤቶች ጋር ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒሰቴር አዳራሽ የግምገማዊ ዓውደ ጥናት አካሄደ፡፡

በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የዋና ዳይሬክተር አማካሪ የሆኑት አቶ ነጋሽ ቦንኬ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (Electronic Government Procurement) በማስተዋወቅ ሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመው፣ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ማለት ተጠቃሚዎች በInformation Technology በመታገዝ ግዥን ከመደበኛ የግዥ ሂደት ወደ ኤሌክትሮኒክ የግዥ ሂደት በመውሰድ መቆጣጠር እንዲችሉ የማድረግ የግዥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም አቶ ነጋሽ ቦንኬ ብዙ የአፍሪካ አገሮች እና በዓለም ላይ ያሉ አገሮች የግዥሥርዓታቸውን ለማሻሻል E-GPን በማሰሪያነት እየተጠቀሙ መሆናቸውን ገልጸው፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲም ከ2010ዓ.ም ጀምሮ ብዙ ስራዎችን በመስራት የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን በማረገገጥ ላይ መሆኑን አሰረድተዋል፡፡

አማካሪው አቶ ነጋሽ ቦንኬ የዛሬው ዓወደ ጥናት PERAGO Information System ባጠናው Business Process Review የመጀመሪያው ረቂቅ ላይ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ አማካሪ ድርጅት የE-GP Information System ለሙከራ በተመረጡ መ/ቤቶች በስራ ላይ ስላጋጠመው ችግሮች እና ሰለሚጠበቁ ሥርዓቶች ለማስረዳት መሆኑን ገልጠዋል፡፡
በሥልጠናው ላይ ለሙከራ ከተመረጡ መ/ቤቶች የተለያዩ ዶክመንቶች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን፣ በወይይቱም ላይ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቂ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
ለአንድ ቀን በቆየው E-GP Business Process Reviewን ዓውደ ጥናት ሰነድ ላይ ኤጀንሲው ሥራ አመራሮች፣ባለሙያዎች እና ለሙከራ ከተመረጡ የፌዴራል መ/ቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት