The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ኤጀንሲው በ2ዐ11 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከመላው ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የ2ዐ11 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ ከመላው የኤጀንሲው ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ጋር ህዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም በመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ አገልገሎት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡ክብርት ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ–ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የስብሰባው ዓላማ በዚህ በ2ዐ11 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ምን አቅደን? ምንስ ፈጸምን? የሚለውን ለመወያየትና በቀጣይ መሰረት ለማስቀመጥ መሆኑን ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል፡፡በመቀጠልም ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በዋናነት እንደሚታወቀው እቅድ ሶስት ሂደቶች (የዝግጅት፣ የትግበራና የማጠቃለያ ምዕራፎች) እንዳሉት እና ከነዚህም በመጀመሪያው የዝግጅት ምዕራፍ ብዙ ስራዎች እንደተሰሩና ማኔጅመንቱም ሰፊ ጊዜ ወስዶ ያለፈውን ገምግሞ ዝግጅቱን ወደ ሰራተኛው ማውረዱን፣ ከዕቅድ ዝግጅት ባለፈ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተገናኝቶ ሥልጠና መሰጠቱን መመሪያዎችንና የሥጋት ተጋላጮች ምንድናቸው? የሚሉት ታይተው መገምገማቸውንና የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ወ/ሮ አበባ ዓለማየሁ የለውጥ ትግበራ ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የኤጀንሲውን የ2ዐ11 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ አመት የዕቅድ አፈፃፀምን በሚመለከት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ኤጀንሲው የ5 አመት ስትራቴጂያዊ እቅድ (ከ2008-2012) አዘጋጅቶ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲተገብር ቆይቶ በ2011 በጀትዓመት ዕቅዱን እንደገና በመፈተሽ አሠራሩን ዘመናዊና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ የትኩረት መስኮችና ግቦችን በማሻሻል የግዥና የንብረት አስተዳደር ሥራዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል የስራ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን አሰረድተዋል፡፡

በመቀጠልም ዳይሬክተሯ የተዘጋጀው ዕቅድ ውጤት ተኮር ሥርዓት መሠረት ወደ ዳይሬክቶሬቶች ከዚያም ወደ ሠራተኛው የወረደ ሲሆን በኤጀንሲው በተደራጁ 17 የ1ለ5 የካይዘንና የለውጥ ሠራዊት ቡድኖች አማካይነት ሳምንታዊ የሥራዕቅድ እየተዘጋጀ አፈፃፀሙን እየተገመገመ ዕቅዱ እንዲተገበር እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ዳይሬክተሯ የ2011 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑት እና ወደ ትግበራ ምዕራፍ በመሸጋገር የተሰሩትን ስራዎችን በማካተት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፣ አስተያየቶችም ተሰጥተዋል፡፡ በተነሱትም ጥያቄዎች ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ እና የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጆንሴ ገደፋ መልስ በመስጠትና የማጠቃለያ ንግግር በማድረግ የጋራ ግንዛቤ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡ለግማሽ ቀን በቆየው የዉይይት መድረክ ላይ የኤጀንሲዉ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብግንኙነትናኮሚዩኒኬሽንዳይሬክቶሬት