The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

በአካባቢ የአየር ንብረት ለውጥና እንክብካቤ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአካባቢ የአየር ንብረት ለውጥና እንክብካቤ ዙሪያ ላይ ያተኮረ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ለመላው የኤጀንሲው ሰራተኞች ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ.ም በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሰጠ፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ የፌደራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጆንሴ ገደፋ በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የአካባቢ ጉዳይ የአጠቃላይ የህዝቡ ጉዳይ እንደሆነ በመግለፅ በአካባቢያችን ያለውን የተፈጥሮ ስጦታ በአግባቡ በመያዝ ኤጀንሲው የተቋቋመበትን አላማ ለማስፈፀም ስራዎችን ሚዛናዊ አድርጎ መያዝ እነደሚገባ በማሳወቅ ውጤታማ የሆነ ውይይት ከተሳታፊዎች እንደሚጠበቅ በማሳሰብ ስልጠናውን ከፍተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአካባቢና የደን ሚኒስቴር ባለሙያ የሆኑት ወ/ት ረሂማ መሀመድ እና አቶ አብርሀም ቸርነት ሥልጠናውን የሰጡ ሲሆን፣አቶ አህመድ አሊ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የቴክኒክ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሥልጠናው ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስልትን የልማት ሞተር አድርጋ እንደምትተገብረው በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ በግልጽ ማሰቀመጧን በመግለፅ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረት አግኝቶ ሊሰራ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ከስልጠናው ውይይት የሚገኙ ግብዓቶች ሊያዙ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአካባቢና የደን ሚኒስቴር ባለሙያ የሆኑት ወ/ት ረሂማ መሀመድ የአየር ንብረት ሙቀት ሳቢ ጋዞች፣ የአየር ንብረት አሉታዊ ተፅዕኖዎቹ ፣ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ፣ ራዕይ ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስልት፣የስልቱ አዘገጃጀት፣ ተቋማዊ ሁኔታ፣ የማጣጣሚያ ስልት እና በማጠቃለያው ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል፡፡

በሚኒስቴሩ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብርሀም ቸርነት በበኩላቸው በሀገራችን የአካባቢ አስተዳደር መቼ ተጀመረ? የአየር ንብረት ለውጥ ክስተቶች እና እንክብካቤው፣የኢትዮጵያ የአካባቢ ፖሊሲ፣ ሕግ…. ይዘት ምን ይመስላል? በአካባቢና ደን ሚኒኒስቴር ምን እየተሰራ ነው?እና የአካባቢና ደን ሚኒስቴር ስልጣንና ተጋባራት ላይ  ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የሚገዙ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ማስቻል፣የአገልግሎት ዘመናቸው ያላለቀ እና ለማለቅ ያልተቃረቡ፣ ወደ ሃገር የሚገቡት ቁሳቁሶች ከአካባቢ ጋር የሚጣጣሙ እንዲሆኑ በማገዝ በወቅቱ እንዲገዙ እና አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል የሚሉት ከኤጀንሲው የሚጠበቁ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ለግማሽ ቀን በቆየው የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአካባቢ የአየር ንብረት ለውጥና እንክብካቤ ዙሪያ ላይ ያተኮረ  የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ላይ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ዳሬክተሮች፣ከፍተኛባለሙያዎች፣ባለሙያዎችና ሌሎች የኤጀንሲው ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡