The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

12ኛው የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን እና 29ኛው የኤች.አይቪ. ኤድስ ቀን ተከበረ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን እና ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጋር በመሆን የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን እና የዓለም አቀፍ የኤድስ ቀን ህዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አዳራሽ በድምቀት አከበረ፡፡

ወ/ሮ እንቁ አሰናቀ ከፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኃላፊ በዓለም ለ27ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ ”በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን መከላከልና ለማስቆም የወንዶች አጋርነትን ማጠናከር” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀንን በሚመለከት፣ጾታዊ ጥቃት እና የሴቶች መብት ከሚለው ተነስተው ስለጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭሪቫን/ ንቅናቄ ታሪካዊ አጀማመር፣ የነጭ ሪቫን ንቅናቄ አስፈላጊነት፣ ጾታዊ ጥቃት (violence) ምንድነው? ጾታን መስረት ያደረገ ጥቃትዓይነቶች፣ጾታዊ ጥቃት በማንና የት ይፈጸማል? ስለሚያስከትለዉ ውጤትና የጥቃቱ መንስኤዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡

በመቀጠልም አሰልጣኟ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት አለም አቀፋዊ ገጽታዎች፣ ጾታዊ ጥቃትበኢትዮጵያ፣ስለህግ ማዕቀፍ፣ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት ሴቶች ሊከበሩላቸው ስለሚገቡ መብቶች፣አለም አቀፍ ስምምነቶች፣የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ፣የሲቪል የፍትህ ሥርዓት፣የተለያዩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ጾታዊ ጥቃትን መከላከልና ምላሽ መስጠት፣ ወ/ት ትሁት ሙሉጌታ በብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን የጤናና ሥነ—ምግብ ፕላን ባለሙያ በዓለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ29ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኤድስ ቀን በማስመልከት አለምአቀፍ የኤድስ ቀን ማክበር ለምን አስፈለገ?ኤች.አይ.ቪበኢትዮጵያ፣ ስለሶስት ዘጠናዎች ግብ(90-90-90)፣ሰለኤች.አይ.ቪ ስርጭት አሳሳቢነት፣ መቀዛቀዙ ሊያስከፍል ስለሚችለውዋጋ እና ስለትኩረት አቅጣጫዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡ለግማሽ ቀን የቆየው የዓለም የኤድስ ቀን እና የዓለም አቀፍ የጸረ—ጾታዊ ጥቃት ቀን የሶስቱም መ/ቤት ሃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት