The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የ10ኛዉን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ

የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴርና ከመንግስት የግዥና የንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጋር በመተባበር ለ10ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ግቢ ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በድምቀት አከበረ፡፡
የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ተ/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጆንሴ ገደፋ  በበዓሉ መክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ፡- “እኛ ኢትዮጵያውያን”  የድህነትና ኋላ-ቀርነት ታሪክ ከሀገራችን ተወግዶ፣ ኢትዮጵያችን በልማትና በዴሞክራሲ ጎዳና በፍጥነት ተራምዳ ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ  መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነውን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ወደ ማይቀለበስ ደረጃ እንዲደርስ፤ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ለውጥ
በማረጋገጥ ሂደት ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎች በማስወገድ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን ለማሳካት በሀገራችን ሰንደቅ አላማ ፊት ቃል እንገባለን፡፡ የሚለውን ቃለ- መሐላ በዓሉን ለማክበር ለተሰበሰቡት ሰራተኞች ቃል አስገብተዋል፡፡
በመቀጠልም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በበዓሉ ታዳሚዎች፣በኢትየጵያ የፌደ ራል ወታደሮች እና  በድምፅ በተቀነ ባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመታጀብ ባንዲራውን የመስቀል ሥነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡
ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም የተከበረውን የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን የሶስቱም መ/ቤት ሠራተኞች በድምቀት አክብረዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት