The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የግንቦት 20 ድል 26ኛውን ዓመት በዓል በድምቀት አከበረ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከመንግሥት የግዥና የንብረት ማስወገድ አግልግሎት ጋር በመተባበር የግንቦት 20 ድል 26ኛውን ዓመት በዓል ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አዳራሽ በድምቀት አከበረ፡፡


አቶ ሰለሞን ዓይኒማር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አግልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር በዓሉን በማስመልከት የሃገራችንን ወደኋላ ያለውን ታሪክና አሁን ያለችበትን ሁኔታ የሚያስረዳ ጽሁፍ የቀረቡ ሲሆን፣ በግንቦት 20 ከተገኙት ትሩፋቶች መካከል ብዝሃነትን ተከተሎ ከተቀረጸው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ዕሴቶች ስለሆኑት ሰለመፈቃቀድ፣  አዲሲቱ ኢትዮጵያ በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የምትገለጽ ሀገር ስለመሆኗ፣ ስለአብሮነትና መልካም ግንኙነት፣ ተደጋጋፊነትና አጋርነት፣ ስለ ሥነ-ልቦናዊ አንድነት፣ ስለመከባበርና መቻቻል ስለ ዲሞክራሲያዊ ዓላማ ማራመድና ሁሉን ነገር በዲሞክራሲያዊ መንገድ ማሰተናግድ እንደሚገባ በሰፊው አብራርተዋል፡፡
በመቀጠልም የዕለቱ የክብር እንግዶች የሆኑት አቶ ይገዙ ዳባ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አግልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና አቶ ጆንሴ ገደፋ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጊዜያዊ ዋና ዳይሬክተር ስለ ግንቦት 20 ታሪካዊ አመጣጥና ሰለአለፉት ሥርዓቶች አስከፊነት ስለፌዴራላዊ ሥርዓት መገንባት፣ አሁን የት ነው ያለነው? ወዴትስ ነው እየሄድን ያለነው? በሚል ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ የጋራ አገር ስላለን የበለጠ አንድነታችንን እያጠናከርን መሄድ እንዳለብንም አሳሰበዋል፡፡

ለግማሽ ቀን በቆየው የግንቦት 20 ድል 26ኛው ዓመት በዓልን የሁለቱም መ/ቤት ሠራተኞች በድምቀት አክብረዋል፡፡


ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት