The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበረ


የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትርና ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጋር በመተባበር ለ9ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓልን በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ዉስጥ ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት አከበረ፡፡በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዋሲሁን  አባተ በዕለቱ በበዓሉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ፡- “እኛ ኢትዮጵያውያን የድህነትና ኋላ-ቀርነት ታሪክ ከሀገራችን ተወግዶ፣ኢትዮጵያችን በልማትና በዴሞክራሲ ጎዳና በፍጥነት ተራምዳ ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነውን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ወደ ማይቀለበስ ደረጃ  እንዲደርስ፤ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ለውጥ በማረጋገጥ ሂደት ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎች በማስወገድ  ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን ለማሳካት በሀገራችን ሰንደቅ አላማ ፊት ቆመን ቃል-እንገባለን” የሚለውን ቃለ- መሐላ በዓሉን ለማክበር ለተሰበሰቡት የሦስቱ ተÌማት ሠራተኞች ፊት ቆመዉ መላዉን ሠራተኛ ቃል አስገብተዋል፡፡መቀጠልም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በበዓሉ ታዳሚዎች፣በፌደራል ወታደሮች እና  በድምፅ በተቀነባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመታጀብ ባንዲራውን የመስቀል ሥነ-ስርዓት ተከናውኗል፡፡በጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም የተከበረውን የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓልን የሶስቱም መ/ቤት ሠራተኞች በድምቀት አክብረዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት