The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ኤጀንሲዉ የመ/ቤቶችን ግዥ ሂደት መለካት ሊጀምር ነዉ

የመንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶችን የግዥ ሂደት መለካት የሚያስችል የግዥ መለኪያ መሣሪያ (key performance indicators guide line tools) በማዘጋጀት ወደ ስራ ለመግባት ዝግጀት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጆንሴ ገደፋ መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ ሰፋፊ መሰረተ ልማትና ትላልቅ ግዥ የሚፈፀምባቸዉ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች የተዉጣጡ በግዥ ላይ የሚሰሩ ኃላፊዎች፣የዉስጥ ኦዲት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር አዳማ በሚገኘዉ ሪፍት ቫሊይ ሆቴል ለሁለት ቀናት በቆየዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ እንደገለፁት የመንግስት ግዥ ከአገሪቱ አመታዊ በጀት ዉስጥ ከ60% እስከ 70% የሚሆነዉ ገንዘብ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በመንግስት ግዥ ሥራ ላይ ስለሚዉል ኤጀንሲዉ የመንግስት ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ ብቻ ለማዋል እንዲቻል የመንግስት ግዥ ግልፅ፣ ቀልጠፋ፣ዘመናዊ፣ዉጤታማ፣ ከአድሎ ነጻ እንዲሁም ተጠያቂነት ያለበት በመሆኑ በሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች፣ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ መስተዳደሮች ከ2009 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ሲለሚሆን ልዩ ትኩረት ሠጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የመንግስት ግዥ መለኪያ መሣሪያዉ (key performance indicators guide line tools) ለሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ መስተዳደሮች በራሣቸዉ ነባራዊ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የተደረገ ሲሆን ከሰፋፊ መሰረተ ልማትና ትላልቅ ግዥ ከሚፈፀምባቸዉ መ/ቤቶች የተዉጣጡ ኃለፊዎችና ባለሙያዎች ጥያቄዎች ተነስተዉ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች መልስ በኤጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር መልስ ተሠጥቷል፡፡
ሰፋፊ መሰረተ ልማትና ትላልቅ ግዥ ከሚፈፀምባቸዉ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች የተዉጣጡ በግዥ ላይ የሚሰሩ ኃላፊዎች፣ የዉስጥ ኦዲት ኃላፊዎች እና የግዥ ባለሙያዎች የግዥ መለኪያ ዘዴዉ (key performance indicators guide line tools) ቀለል ብሎ የተዘጋጀና ከዕለት ዕለት ስራችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለዉ መሆንና ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆንና ኤጀንሲዉ ሊመሰገን እንደሚገባና ለቀጣይ ስራቸዉ የግዥ መለኪያ መሣሪያዉ አጋዥ እንደሚሆንላቸዉ አያይዘዉ ገልፀዋል፡፡
ለሁለት ቀን በቆየዉ ግዥ መለኪያ መሣሪያ (key performance indicators guide line tools) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ከመ/ቤቶቹ የኦዲት ኃላፊዎች ጋር ትኩረት በመስጠት ለጋራ ዓላማ ኤጀንሲዉ ክትትል፣ቁጥጥር እና ድጋፍ ለማጠናከር ተባብሮ ስለሚሠራ ለሚዘገዩ የግዥ ፕሮጀክቶችና ለሚጓተቱ ግዥዎች መፍትሄ ይሆናል ተብሎ ይታመናል፡፡