The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ኤጀንሲዉ የተቆጣጣሪነት ሚና ካላቸዉ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ተፈራረመ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በሐምሌ 26/2008 ዓ.ም ከፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እና ከኢትዮጵያ ግንባታ ፕሮጀክቶች መረጃዎች ተደራሽነት(CONSTRUCTION SECTOR TRANSPARENCY INITIATIVE-ETHIOPIA (COST-ETHIOPIA)) ጋር በጋራ ተባብሮና ተደጋግፎ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የየተÌማቱ ኃላፊዎች በተገኙበት በካፒታል ሆቴል ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አበበ እንደተናገሩት ከአገሪቱ በአመት በጀት ዉስጥ ከ60% እስከ 70% የሚሆነዉ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በመንግስት ግዥ ሥራ ላይ እንደሚዉልና ከዚህ ዉስጥ ለግንባታ ፕሮጀክቶች የሚመድበዉ በጀት ደግሞ ከፍተኛ በመሆኑ በጋራ አብሮ መስራቱ የተሻለ ዉጤት እንደሚያመጠና ኤጀንሲዉ ስምምነት ሰነዱን(MEMORUNDUM OF UNDERSTANDING) ሲፈርም በሙሉ ፍቃደኝነትና ፍላጎት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ፀጋዬ አበበ አያይዘዉም የህዝብ ሃብት ለታለመለት ዓላማ እንዲዉልና በኢትዮጵያ የሚሰሩትን የግንባታ ፕሮጀክቶች ለህዝብ ይፋ በማድረግ የሚሰሩትን የግንባታ ፕሮጀክቶች ግልፅነትና ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱ(MEMORUNDUM OF UNDERSTANDING) ላይ የተገኙት የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌይማን፣ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እና ከኮስት ኢትዮጵያ(CONSTRUCTION SECTOR TRANSPARENCY INITIATIVE - ETHIOPIA ወይም COST-ETHIOPIA) የተገኙ ኃላፊዎች አብዛኛዉ በአገሪቱ ዉስጥ የሚከናወኑ የግንባታ ፕሮጀክት ስራዎችን ግልፀኝነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን የግዥ ሂደቱን ለህዝብ ይፋ በማድረግ ህብረተሰቡ ጠያቂ የሚሆንበትን ስርዓት ለመገንባት የጋራ ስምምነት ፊርማዉ ትልቅ ዕገዛ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል፡፡
ከኤጀንሲዉ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት