The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

በመንግስት የፋይናንስ፣ግዢና ንብረት አስተዳደር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በመንግስት ፋይናንስ እና የግዥ ንብረት አስተዳደር ላይ ያተኮረ ስልጠና በሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እያካሄደ ነው፡፡
የመንግስት ወጪ አሰተዳደር ቁጥጥር ሪፎርም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሳ መሐመድ እንደተናገሩት በመንግስት ወጪ አሰተዳደርና ቁጥጥር ሪፎርም ፕሮግራም ለረዥም አመታት በተበታተነ መልኩ ሲሰጡ የነበሩ ስልጠናዎችን በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ተቋማዊ በሆነ መንገድ በመቀየር በተከታታይነት ስልጠናዎችን ለመስጠት ያስችላል፡፡የዚህ ስልጠና ዋነኛ አላማ የመንግስት ፋይናንስ አሰተዳደርን አቅም ግንባታ በማሳደግ የመንግስት የፋይናስ አሰተዳደርን ይበልጥ ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡ የስልጠናው ትኩረት በመንግስት የፋይናስ አሰራር፣በጥሬ ገንዘብና የክፍያ አፈጻጸም፣በመንግስት ግዢና ንብረት አሰተዳደር እንዲሁም በውስጥ ኦዲት ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ነው፡፡በሌላ በኩል በአዲሱ የፋይናንስ አሰተዳደር አዋጅና በፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ዙሪያ ላይ ባለሞያዎቹ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይደረጋል ሲሉ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙሉጌታ ደበበ የሚሰጠው ስልጠና ባለሞያዎች በመንግስት ፋይናንስ አሰተዳደር ላይ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይደረጋል ብለዋል፡፡
ስልጠናው ከ33 ዩኒቨርሲቲዎችና ስምንት የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ለተወጣጡ ከ300 በላይ ባለሞያዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ስልጠናው በአራት ዙሩች እንደሚቀጥልም ታውቋል፡፡
ምንጭ፡-Ministry of Finance and Economic Cooperation of Ethiopia's photo.