የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የሴቶችን ቀን በደማቅ ሁኔታ አከበረ።

*******************************************************
(መጋቢት 02/2018 ዓ.ም)፤ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ “ለማግኘት መስጠት” በሀገራችን ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ “50 ዓመት የሴቶች ድምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የሴቶች ቀን በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።
በዓሉ በፓናል ውይይት እና በስልጥና የተከበረ ሲሆን እለቱን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ በዓሉ ታስቦ የሚውል ብቻ ሳይሆን የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማጉላት እንደሚገባ አሳስበው አሁን ላይ የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፍ እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት አያይዘውም ሴቶች ድርብ ሀላፊነት ያለባቸው መሆኑንና ሴቶች ላይ መስራት ትውልድን ማስቀጠል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በእለቱ ከበዓሉ ባለፈ በስሜታዊ ብስለት (Emotional intelligence) ላይ ለሴቶች ፎረም አባላት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት አቶ አራጋው ሲሳይ እንደገለጹት የስኬት ቁልፉ ምስጢር ስሜታዊ ብስለት መሆኑንና በተለይም ራስን ማወቅ፣ ማህበራሰብን/ከባቢን ማወቅ፣ ራስን መግዛት እና ግንኙነትን ማዳበር የስኬት ምንጮች መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
ከበዓሉ በተጨማሪ ባለስልጣኑ በጡረታ የተሰናበቱ ሦስት ባለሙያዎችንም በክብር ሸኝቷል።








0 Comments