የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) ውጤታማነትን ለማስቀጠል ላለፉት ስድስት ወራት ማሻሻያዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ጥራትና ቅልጥፍና ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት እና ከተገልጋዩ ማህበረሰብ ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይትና ምክክር እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ከፌዴራል የመንግስት ተቋማት ሀላፊዎች፣ ከግዥ ዳይሬክተሮችና ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል። ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የመንግስት ትልቁ በጀት ለግዥ አገለግሎት የሚውል በመሆኑ ይህን በጀት በስርዓት መምራትና የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) ትልቅ ሀግራዊ ሚናን እየተወጣ የሚገኝና ውጤታማነቱን ለማስቀጠል ላለፉት ስድስት ወራት ማሻሻያዎች ሲደረጉ እንደቆዩ ገልጸዋል።




0 Comments