ከከፍተኛትምህርትተቋማትአመራሮችጋርሲካሄድየነበረውየምክክርመድረክበተሳካሁኔታተጠናቀቀ።

(ሀምሌ 23/2018 ዓ.ም)፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በውይይት መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዘዳንቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ነበሩ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በኢጂፒ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ያፌት መኮንን የቀረበ ሲሆን የዘላቂ ግዥ አፈጻጸም ማኑዋል እና የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝ፣ አጓጓዝ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ ማኑዋል በመንግስት ግዥና ንብረት ማሻሻያ እና አቅም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ተጓዴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተጠናው የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝ፣ አጓጓዝ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ ጥናት በጥናት ቡድኑ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ተሳታፊዎቹ በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በንቃት የተሳተፉ ሲሆን በተለይም ከመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) ስርዓት፣ አጠቃላይ ከግዥ አካሄዶች፣ ዘላቂነት ያለው ግዥን እውን ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ እና ከአደገኛ ቆሻሻ አያያዝ፣ አጓጓዝ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ ጥናት ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችንና ገንቢ ሃሳቦችን አንስተዋል።
በቀረበው ጥናት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በጥናት ቡድኑ እንዲሁም በሌሎች ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ከባለስልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች አስፈላጊው ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የቀረቡት ሰነዶችና የተደረጉት ውይይቶች ወደፊት የሚከናወኑ የጋራ ሥራዎችን በላቀ ደረጃ ለማስፈጸም ያላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ገልጸዋል።






0 Comments