Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ የሪፎርም የትግበራ ምዕራፉን በብቃት እየተገበረ እንደሚገኝ ተገለጸ።

(ህዳር 14/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የሪፎርም የትግበራ ምዕራፍን በብቃት እየተወጣ ነው ሲሉ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሯ ይህን የተናገሩት የተቋሙን የአገልግሎት ስነ- ምድብ (Service Taxonomy) በሚመለከት ከባለስልጣኑ ሰራተኞች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።

ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው በትግበራ ምዕራፉ ይሰራሉ ተብለው ከተያዙ ጉዳዮች አንዱ የዲጂታል ስራዎች ማስፋት መሆኑን አንስተው በዚህም የአገልግሎትን ጥራትና ቅልጥፍና ሊጨምሩ የሚችሉ የዲጂታል ስራዎች መልማታቸውን አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአደረጃጀት ስራዎች፣ የአቅም ግንባታ ስራዎች፣  ማኑዋሎች፣ የስልጣን ሞጁሎች፣ የአገልግሎት አስጣጥ ጥራትንና ቅልጥፍናን ሊያሳድጉ የሚችሉ የአሰራር ስርዓቶች፣ መዘጋጀታቸውን አብራርተዋል።

በተቋሙ የአገልግሎት ስነ- ምድብ (Service Taxonomy) ላይ ገለጻ ያደረጉት የባለስልጣኑ ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳን ኤል ገረመው በበኩላቸው ባለስልጣኑ የሚሰጠው አገልግሎት ስነ ምድብ የተዘጋጀለት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድም እንደወጣላቸው አመላክተዋል። አቶ ዳንኤል በገለጻቸው ባለሙያው የሚለካው በሚሰጠው አገልግሎት ብቻ ሳይሆን አገልግሎት አሰጣጡ ስታንዳርዱን መሰረት በማድረግ የተሰጠ መሆኑና ስታንዳርዱ በሚያስቀምጠው ጊዜ፣ መጠን እና ጥራት ልክ መሆኑን በማረጋገጥ ጭምር መሆኑን አመላክተዋል።

በመጨረሻም ከሰራተኛው የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን በክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እና በአቶ ዳን ኤልገረመው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል።   

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *