Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

በኮንትራትማኔጅመንትዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠናተጠናቀቀ።

(ሀምሌ 11/2018 ዓ.ም)፣ በኮንትራት ማኔጅመንት (ውል አስተዳደር) ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ሀገር አቀፍ የስልጠና መድረክ በስኬት ተጠናቋል። በድረኩ ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቅሌ ባደረጉት ንግግር ስልጠናው በዘርፉ ያሉ የአሰራር ክፍተቶችን ለመሙላት እና የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።

ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የገጠር መንገድ ፕሮጀክቶች የህዝብን ህይወት የሚቀይሩ መሰረታዊ የልማት ፕሮግራሞች መሆናቸው፣ የኮንትራት ማኔጅመንት አሰራርን ማዘመን እና ከጨረታ ሰነድ ዝግጅት መጀመር አስፈላጊ መሆኑ፣ የዋጋ ማሻሻያ (Variation Order) እና የጊዜ ማራዘሚያ (Time Extension) ቁጥጥር አስፈላጊ መሆኑ፣ የፕሮጀክት ጥራት ቁጥጥር እና የተቋማት ቅንጅት ለማንኛውም ስራ ስኬት መሰረት መሆኑ፣ የግዥ ህግ ልማትን እንደማያደናቅፍ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቷል።

ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በማጠቃለያቸውም ከዚህ ስልጠና የተገኙ እውቀቶችና የጋራ ተሞክሮዎች ወደ ስራ ሲመለሱ በሚገባ ሪቪው (Review) ሊደረጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። የስልጠናውና የሁለት ቀኑ ውይይት ትክክለኛ ውጤት ሊለካ የሚችለው በስራዎች ጥራት፣ የፕሮጀክት መዘግየት ጊዜ ሲቀንስ፣ የተሻሻለ የኮንትራት አስተዳደር ሲኖር እና በተቋማት ቅንጅት አማካኝነት የህዝባችንን እርካታ ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ በመሆኑ ሁሉም አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *