The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ WSU-02-2013 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2020
Bid Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡- ብ.ግ.ጨ.ወሶዩ/02/13

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2013 በጀት ዓመት ለዋናው ፣ለቴክኖሎጂ እና ለኦቶና ካምፓስ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚዉል ነጭ ጤፍ እና ሽሮ አተር ፤አትክልት ፤ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ እና ያልተፈጨ በርበሬ እና የማገዶ እንጨት ለአንድ ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የዕቃዎች ዝርዝር የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን

ለዋናው፣በቴክኖሎጂ  እና ለኦቶና ካምፓስ  ካምፓስ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚዉል፤

ምድብ -1 ለነጭ ጤፍ እና ሽሮ አተር----------------------------------- ብር 150,000.00

ምድብ -2 ለአትክልት ----------------------------------------------------- ብር 100,000.00

ምድብ -3 ለምግብ ሸቀጣሸቀጥ ------------------------------------------- ብር 100,000.00

ምድብ -4 ለበርበሬ ያልተፈጨ  ----------------------------------------- ብር  70,000.00

ምድብ -5 ማገዶ እንጨት ------------------------------------------------ ብር 80,000.00

በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በሚወዳደርበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ TIN ሰርተፊኬት፣ እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ  ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  2. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ በየምድቡና በየንግድ ዘርፍ ያላቸዉን ሰነዶች ኮፒዉንና እንድሁም ዩኒቨርሲቲዉ ባዘጋጀዉ  ጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ  በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒዉን  በየምድቡ ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  3. ተጫራቾች በጨታው ለመካፈል የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ  በባንክ በተመሰከረ የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO  በሚወዳደሩበት ምድብ በተጠየቀው  ገንዘብ መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ከአንድ ምድብ በላይ የሚወዳደር ተጫራች በሚወዳደርበት ምድብ  ብዛት CPO / የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  5. ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  አስከ 15ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ዘውትር በሥራ ሰዓት በአት/ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000018154278 በወላይታ ሶዶ ዪነቨርሲቲ  ስም ለእያንዳንዱ ምድብ  የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)  በመክፈል ኦርጅናል የባንክ ስልፕ ይዘዉ በመምጣት ከዩኒቨርስቲው ግልጽ ጨረታ ሰነድ በግዥ ዳይሬክቶሬት  ቢሮ እና በአዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ መዉሰድ  ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግተዉ በዕለቱ 4.፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸዉ  በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በአስተዳደር ሕንጻ 1ኛ ፎቅ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል ፡

7. ሁሉም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO/ ባንክጋራንቲ/ የሚመለስላቸው አሸናፊ ድርጅቶች   ውሉን ሲፈራረሙና የውል ማስከበሪያ 10% C.P.O ሲያሲይዙ ይሆናል፡፡

  1. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913491657/0911014555/0913531451 ፋክስ 0465515113

ማሳሰቢያ ፡ የጨረታ ሠነዱን ከዚህ በታች በተገለፀዉ አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡

1. በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ

2. በአዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ  አድራሻ ፤- ከመገናኛ አንድ ኪሎ ሜትር  ገባ ብሎ  ቦሌ ክ/ከተማ ጀርባ አምቼ ካምፓኒ በእርሻ ምርምር ወይም እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን መንገድ  ላይ ስልክ ቁጥር - 0913790195 / 0912881430

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 09/01/2021
Bid Closing Time 10:00 AM
Expected Award Date30/01/2021
Extended To
Reason for extension