The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ PPS/NVP-1FBI/13/09/2014 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2022
Bid Description

 

የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ ዓይነት ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPS/NVP-1FBI/13/09/2014

የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስቲል) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 80,000 ኪሎ ግራም፤ አልሙኒየም ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 300 ኪሎ ግራም፤ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የቁርጥራጭ ብረታብረቶችን ዝርዝር መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣

4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ዓይነት ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ማለትም (ስቲል) ብር 160‚000.00 ለአልሙኒየም ብር 450.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በመንግሥት ግዥ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 007 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርቱ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

6. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣

8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከአገልግሎቱ ጋር ውል መፈራረምና፤ በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠው የእያንዳንዱ የቁርጥራጭ ብረታብረት ዓይነት ግምታዊ ጠቅላላ መጠን ተወስዶ ባሸነፉበት የ1 ኪሎ ግራም ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በመንግሥት ግዥ አገልግሎት ስም CPO አዘጋጅተው መክፈል አለባቸው፡፡ በተጨማሪም የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶቹ ግምታዊ መጠን በርክክብ ወቅት በሚዛን ፕሪንት አውቱ ንባብ ከሚገኘው ትክክለኛ የቁርጥራጭ ብረታ ብረት መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውሉ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት በልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን ከአገልግሎቱ ተመላሽ ሊደረግለት የሚገባ ገንዘብ ካለም በትክክለኛው የገንዘብ መጠን ልክ ሲፒኦ አሰርቶ በመምጣትና በመክፈል ቀደም ሲል ግምታዊ መጠኑ ተሰልቶ ያስያዘው የክፍያ ሲፒኦ በአገልግሎቱ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ፣ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎች በመሸፈን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቱ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን እንዲመዘን፣ ሆኖም የመንግስት የምድር ሚዛን ካልተገኘ በከተማ ውስጥ ወይም በቅርብ እስከ 25 ኪሎ ሜትር ራድየስ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የግል ድርጅት በማስመዘን ውል በፈረሙ በ20 የሥራ ቀናት ዉስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡

11. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122-37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

13. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 

የመንግሥት ግዥ አገልግሎት

አዲስ አበባ

Bid Attachment

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማስታወቂያ.doc

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 13/06/2022
Bid Closing Time 10:00 AM
Expected Award Date30/06/2022
Extended To
Reason for extension