The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ NCB/WSU/01/11 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2019
Bid Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግ.መለያ ቁጥር፡- NCB/WSUW:-01/11

  1. የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ፣ በኦቶና ግቢ እና በኦሞቲክ ግቢ የጥበቃ ቤት እና አጥር ግንባታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመወዳደር ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው  መስፈርቶች ፡-

  1. በዘርፉ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN/ ሠርቲፊኬት፣ በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ እና ተጫራቾች በኤጀንሲው ድረ ገጽ ምዝገባ  ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  2. ተጫራች የሥራ ተቋራጭነት ሥራ እንዲሰራ በሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር የተሰጠውን ደረጃ የተጠየቀውን GC-5/ BC-4 ወይም ከዚያ በላይ  ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  3. መልካም የሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  4. ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 21ኛዉ ቀን ድረስ ዘውትር በሥራ ሰዓት ከዩኒቨርስቲው ዋናዉ ግቢ በአስተዳደር ህንጻ በ1ኛዉ ፎቅ ከጨረታ ሠነድ ዝግጅት ቢሮ ለሠነዱ የማይመለስ  ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በአት/ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000018154278 በዪነቨርሲቲው ስም በመክፈል  መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታዉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ አስከ በ21ኛዉ ቀን በ4፡00  ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በአስተዳደር ህንጻ በ1ኛዉ ፎቅ ይከፈታል፡፡
  6. 21ኛዉ ቀን የሚዉለዉ በሰንበት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ  ጨረታዉ የሚከፈተዉና የሚዘጋዉ በሚቀጥለዉ ሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሠዓት መሠረት ይሆናል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የሥራ ሳይት ማየት ካለበት ከውድድሩ በፊት በራሱ ወጪ ማረጋገጥ ይችላል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመካፈል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO/ BANK GUARANTY /CASH ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

ተ.ቁ

የግንባታዎች ዓይነት

የሚጠይቀው ደረጃ

የጨረታ ማስከበሪያ ብር

ግንባታዎች የሚከናወኑበት ቦታ   በሶዶ ከተማ ዉስጥ

01

የአጥር እና ጥበቃ ቤቶች ግንባታ

GC-5 / BC-4 ወይም

ከዚያ በላይ

100,000.00

በዋናው ግቢ፤  በኦቶና ግቢ እና በኦሞቲክ ግቢ

 

  1. የመጫረቻ ሰነዱን የነጠላ ዋጋዉና የጠቅላላ ዋጋቸውን ድምር በሚነበብ ጽሑፍ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ የፋይናንሻል እና የቴክኒካል ኦርጅናሉን እና እያንዳንዳቸውን ሁለት ኮፒዎችን ጋር ለየብቻ  በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በመጻፍ ከላይ እስከተገለጸዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት  ባለው ጊዜ ውስጥ  ገበያ ጥናትና ግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን  ማስገባት አለባቸው ፡፡
  2. ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም ፡፡
  3. የሥራው ዲዛይን ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ የቀረበ ስለሆነ ማየት ይቻላል ፡፡
  4. አሸናፊው ተጫራች ውል ከፈረመ በኋላ ለተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል
  5. ዩኒቨርስቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046551-46-15 ወይም 0913491657  ፋክስ 0465515113
Bid Attachment

construction.pdf

Mode of procurement ICB
Bid Closing Date 29/04/2019
Bid Closing Time 10:00 AM
Expected Award Date29/05/2019
Extended To
Reason for extension