The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ DBU033/2008 ]
Procurement Type Works
Fiscal Year 2015
Bid Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DBU033/2008

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ልዩ ልዩ ግንባታዎች ማለትም፡-

ምድብ-1 (አንድ)፡-የድህረ-ምረቃ ኮምፕሌክስ ህንፃ ግንባታ ደረጃ አንድ (1)  ቢሲ (BC) ወይም ጂሲ (GC)

ምድብ-2 (ሁለት)፡-የተማሪዎች አገልግሎት ፣ የሬጅስትራር ፣ የርቀትና ተከታታይ ትምህርት ህንፃ ግንባታ ደረጃ ሁለት (2) እና በላይ  ቢሲ (BC) ወይም ጂሲ (GC) እና

ምድብ-3 (ሶስት)፡-የአፈር ላብራቶር ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ስቶር ህንፃ ግንባታ ደረጃ ሁለት (2) እና በላይ  ቢሲ (BC) ወይም ጂሲ (GC)  በሆኑ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-

1.   ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ፣ የቫት ሰርተፍኬት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  1. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ120 ቀናት የሚቆይ ብር

ለምድብ-1 (አንድ) ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/

ለምድብ-2 (ሁለት) ብር 213,000 /ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ብር)

ለምድብ-3 (ሶስት) ብር 240,000 /ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር/

በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም የመድህን ዋስትና እንደ ምርጫቸው በአንዱ ከዋናው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ (Tecinical Document) ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ  ብር) በዩንቨርስቲው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ወይም 2 በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-10 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ (Financial Document) ዋናና ቅጅ (original and copy) እና ቴክኒካል ሰነድ (Techinical Document) ዋናና ቅጅ  (Original and Copy) ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎኘ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር G-10  ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 የቴክኒካል ሰነድ ፖስታ በውጭና ህዝብ ግንኙነት የመሰብሰቢያ አደራሽ በግልፅ የሚከፈት ሲሆን የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ (ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል)፡፡  የዋጋ ሰነድ የያዘ ፖስታ ሳይከፈት ሁሉም ተጫራቾች እና ታዛቢዎች በተገኙበት በሌላ ሳጥን ታሽጎ የቴክኒካል ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኃላ በጨረታው ላይ ለተሳተፉት ለሁሉም ተጫራቾች የመክፈቻውን ቀን በደብዳቤ በማሳወቅ የምንከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  5. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡
  6. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ከላይ ከተጠቀሱት ምድቦች (ግንባታዎች) መርጠው በአንዱ ላይ ብቻ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት በስልክ ቁጥር 0118494101 ወይም ግዥ ቡድን 0118959756 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 29/12/2015
Bid Closing Time 10:00 AM
Expected Award Date29/01/2016
Extended To
Reason for extension