The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ 05/2010 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2018
Bid Description

በፍርድ ቤት ውሳኔ የሠጠባቸውን የተለያዩ የኅትመት ማሽነሪዎችና ንብረቶች ለመሸጥ ታኅሣሥ 26 ቀን 2010 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2010

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በፍርድ ቤት ውሳኔ የሠጠባቸውን የተለያዩ የህትመት ማሽነሪዎችና ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 001 በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 30.00 /ሠላሳ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ቦታ በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖሩባቸዋል፡፡ የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያልያስያዘ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
  4. አንድ ተጫራቾች በጥቅልም ሆነ በነጠላ ማስያዝ ከሚገባው የጨረታ ማስከበርያ አሳንሶ ቢያቀርብ ተቀባይነት የሚኖረው ልዩነቱ ከብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ያልበለጠ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
  5. የጨረታ ሳጥኑ  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት  ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን  በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የእረፍት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት  ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖሩባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣
  7. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122 37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

10. አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 22/01/2018
Bid Closing Time 10:00 AM
Expected Award Date22/01/2018
Extended To
Reason for extension