The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

News

በመንግስት ንብረት አወጋገድ ሥርዓት ላይ አዲስ መመሪያ ወጣ

ተቋማት በዓመት እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ንብረቶችን ማስወገድ እንዲችሉ የሚፈቅድ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ::

ተቋማት በዓመት እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ንብረቶችን ማስወገድ እንዲችሉ የሚፈቅድ መመሪያ መዘጋጀቱን የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሐጂ ኢብሳ እንደገለፁት፤ ቀደም ሲል የነበረው መመሪያ በርካታ ክፍተት ስለነበሩበት ተቋማት ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ዕቃዎች ማስወገድ ላይ ችግር ፈጥሮባቸው ቆይቷል።

አዲስ የተቋቋሙ መሥሪያ ቤቶች ካልሆኑ በስተቀር ነባር ተቋማት በርካታ ንብረቶችን ያለ አገልግሎት አከማችተው እንደሚገኙ ያመለከቱት አቶ ሐጂ፣ ግብና፣ ጤና፣ ገንዘብ፣ ንግድ፣ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተቋቋሙበት ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ ንብረቶችን አጠራቅመው እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

አዲሱ መመሪያ ከዚህ በፊት በነጠላ እስከ አንድ ሺህ ብር በዓመት ውስጥ ደግሞ እስከ መቶ ሺህ ብር የሚያወጡ ንብረቶችን ተቋማት እንዲያስወግዱ ይፈቅድ እንደነበር አመልክተው፣ በተሻሻለው መመሪያ በነጠላ ዋጋ አምስት ሺህ በዓመት ደግሞ እስከ ግማሸ ሚሊየን ብር ማስወገድ እንዲችሉ ሥልጣን ይሰጣቸዋል ብለዋል።

የተሻሻለው መመሪያ ተከማችተው የሚገኙ ንብረቶችን በዘላቂነት ለማስወገድና ወደፊት ክምችት እንዳይኖር እንደሚያደርግ ጠቁመው፣ መመሪያው በገንዘብ ሚኒስቴር ተፈርሞ በ185 የፌዴራል ተቋማት መሠራጨቱን አስታውቀዋል።

እንደ ተሽከርካሪ፣ ማሽነሪና ቁርጥራጭ ብረቶች ያሉ ንብረቶችን በቀጥታ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር እንደሚወገድ የገለፁት አቶ ሐጂ፣ አነስተኛ ዋጋ ያላቸውን ደግሞ ተቋማት በራሳቸው የሚያስወግዱበት ሥልጣን ይኖራቸዋል ማለታቸው ተዘግቧል።

የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ከሚያዝያ 4-8 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደውን የንብረት ምዝገባ ሳምንትን በማስመልከት ለተመረጡ መ/ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ 31 ለሚሆኑ ለተመረጡ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ከሚያዝያ 4-8 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደውን የንብረት ምዝገባ ሳምንትን በማስመልከት መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በገንዘብ ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ፡፡

ክቡር አቶ ሃጂ ኢብሳ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ስብሰባውን የከፈቱ ሲሆን፣ በመክፈቻው ንግግር ላይ እንደተናገሩት ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው የመንግስትና የህዝብ ሀብት በየቦታው ወዳድቆ በፀሀይና በዝናብ ምክንያት በመበላሸት ለብክነት እየተዳረጉ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በመቀጠልም ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህ እየባከኑ ያሉትን ንብረቶችን በመመዝገብ በሽያጭ ወደ ገንዘብ የሚቀየሩትን ለመቀየርና የሚወገዱትን ለማሰወገድ ከሚያዝያ 4-8 ቀን 2013ዓ.ም በሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች የሚካሄደውን የንብረት ምዝገባ ሳምንትን በሚመለከት ዐቢይ ኮሚቴ ሆነው ለተመረጡ መ/ቤቶች ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፐሮግራም በኤጀንሲው መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

አቶ ነጋሽ ቦንኬ የዋናው ዳይሬክተር አማካሪ አጭር ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ያለ አገልግሎት የተከማቹ የመንግስት ንብረቶች ምዝገባ ንቅናቄን በሚመለከት ስለንቅናቄው ዓላማ እና የሚጠበቅ ውጤት፣ያለ አገልለግሎት የተከማቹ ንብረቶችን ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይ በኤጀንሲው የተዘጋጀ አጭር የቪዲዮ ማሳያ፣ የቅድመ ምዝገባ ምዕራፍ ሥራዎች፣ በምዝገባ ምዕራፍ የሚከናወኑ ስራዎች፣ በድህረ ምዘገባ ምዕራፍ የሚከናወኑ ስራዎች እንዲሁም ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ ግዥን መለወጥ ማለት ሃገርን መለወጥ እንደሆነና ግዥ ማለት ንብረት ማለት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡አቶ ወልደአብ ደምሴ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በውይይቱ ላይ በርካታ ጉዳዮች መነሳታቸውን ገልጸው፣ የንቅናቄው ዓላማ እነዚህን ጉዳዮች  ለመፍታት አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ ከተሳታፊዎች ገንቢ የሆኑ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ጥያቄዎችም ተጠይቀው መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው

ከሚያዚያ 4 እሰከ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ያለ አገልግሎት ተከማችተው የሚገኙ የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳር ኤጀንሲ ተገልጿል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ንቅናቄ ዙሪያ የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ ውይይት ተደርጓል፡፡ በቀጣይም ንብረቶቹ ከተመዘገቡ በኋላ ለተጠቃሚ አካላት በማስተላለፍ እና በሽያጭ በማስወገድ ላይ መንግስት በአትኩሮት እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓለማ ሊውል፤ ሲወገድም ለመንግስት ጥቅም ሊያስገኝ በሚያስችል መልኩ ሊወገድና ተቋማት በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ሊተገበር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በገንዘብ ሚኒስቴር የተካሄደው ውይይት ዓላማ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በመለየት፣ የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማመንጨት እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ጭምር ያለመ ነው፡፡

 

የኢፌድሪ የመ.ግ.ን.አ.ኤ.የህዝብ ግንኑነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው

ከሚያዚያ 4 እሰከ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ያለ አገልግሎት ተከማችተው የሚገኙ የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳር ኤጀንሲ ተገልጿል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ንቅናቄ ዙሪያ የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ ውይይት ተደርጓል፡፡

በቀጣይም ንብረቶቹ ከተመዘገቡ በኋላ ለተጠቃሚ አካላት በማስተላለፍ እና በሽያጭ በማስወገድ ላይ መንግስት በአትኩሮት እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓለማ ሊውል፤ ሲወገድም ለመንግስት ጥቅም ሊያስገኝ በሚያስችል መልኩ ሊወገድና ተቋማት በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ሊተገበር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር የተካሄደው ውይይት ዓላማ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በመለየት፣ የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማመንጨት እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ጭምር ያለመ ነው፡፡

በአቅራቢነት ስለመመዝገብ

በኤጀንሲያችን ድረ-ገጽ ላይ በአቅራቢነት በቀላሉ ለመመዝገብ እንዲችሉ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የአጠቃቀም ማኑዋል (User Guide for Supplier) በቅድሚያ መመልከት እንዳለብዎት አይርሱ፡፡ በመመሪያው መሠረት ምዝገባዎን ያከናውኑ፡፡

More Articles...