The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የፌደራል መንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር  ኤጀንሲ ለንግዱ ማህበረሰብ፣ ለነጋዴ ሴቶች ማህበር፣ለጠቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በግዥ አፈፃፀም ዙሪያ ሚያዚያ 26 ቀን 2007 ዓ.ም  በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ፡፡
በኤጀንሲው የመንግስት ግዥና ንብረት የኦዲትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታደለ ነጋሽ ሥልጠናውን የሰጡ ሲሆን የሥልጠናው ዋና ዓላማ ግዥ ፈፃሚና አቅራቢዎች ተፈላላጊ በመሆናቸው በግዥ አፈፃፀም ሥርዓትና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን የግንዛቤ ዕጥረት ለመቅረፍና እንዲ ሁም ግዥ ከፍተኛ የመንግስት በጀት ስለሚይዝ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገውና የተ ሻለ የግዥ ሥርዓት ለማስፈን ከፍተኛ ጠቀ ሜታ ያለው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
አሰልጣኙ የመንግስት ግዥ ስለሚመራባቸ ው ህጎች፣ ስለመንግስት ግዥ መርሆዎች፣ ተግባርና ኃላፊነት፣በመንግስት ግዥ አፈፃፀ ም  ሊኖር ስለሚገባ ሥነ ምግባር፣ስለ ግዥ ዕቅድ፣ ስለ ግዥ ዘዴዎች፣ስለ መደበኛ ጨረታ ሰነድ ይዘት አጠቃቀምና ስለ ጨረታ ግምገማ በዝርዝር ገለፃ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ሂደት የሚቀርብ አቤቱታና የጥፋጠኝነት ሪፖርት እንዴት እንደሚቀርብና አቤቱታ ዎች በማናቸውም የግዥ ሂደት የሚቀርቡ መሆናቸውንና ቅሬታ ዎቹ የሚቀርቡት ከእጩ ተወዳዳሪዎች፣ ከተጫራቾች እና አልፎ አልፎ ከጥቆማ አቅራቢዎች መሆና ቸውን አስታውቀዋል፡፡
በቀረበው ገለፃና ማብራሪያ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ሰልጣኞችም በበኩላቸው ስልጠናው ጥሩ አቅም እንደፈጠረላቸውና የነበረባቸውን ክፍተት ለመሙላትና ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት በየመ/ቤታቸው ወደ ተግባር ለመለወጥና ከፌደራል መንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በቆየው በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥል ጠና ላይ ኃላፊዎች፣ተወካዮችና ባለሙያ ዎች የሥልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ከ.ፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት