The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

በመንግሥት ግዥ አፈጻጸም ዙሪያ ለፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ሥልጠና ተሰጠ

በፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በግዥ አፈጻጸም ዙሪያ ከሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ ሰልጣኞች ከየካቲት 2 እስከ የካቲት 6/2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለአምስት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
የሥልጠናው ዓላማም በዋናነት በፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች በግዥ አፈጻጸም ሥርዓትና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍና እንዲሁም ግዥ ከፍተኛውን የመንግሥት በጀት ስለሚይዝ ጥንቃቄ አንደሚያስፈልገውና የተሻለ የግዥ ሥርዓት ለማስፈን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነ ተገልጿል፡፡


አሰልጣኞቹ አቶ ታደለ ነጋሽ የመንግሥት ግዥና ንብረት የኦዲትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና አቶ ገበያው ይታይህ ከፍተኛ የግዥ ጥናትና መረጃ ትንተና ባለሙያ ስለመንግሥት ግዥ አጠቃላይ ገጽታ፣ የመንግሥት ግዥ ምንድነው? የመንግሥት ግዥ ስለሚመራባቸው ሕጐች፣ ስለዓለም አቀፍ ግዴታዎች፣ ስለመንግሥት ግዥ መርሆዎች፣ ተግባርና ኃላፊነት፣ በመንግሥት ግዥ አፈጻጸም ሊኖር ስለሚገባ ሥነ ምግባር፣ ስለ ግዥ ዕቅድና ዑደት፣ ስለግዥ ዓይነቶች፣ ስለ ጨረታ፣ ስለ ግዥ ዘዴዎች፣ ስለ ቴክኒክ ፍላጐት መግለጫ አዘገጃጀት፣ ስለ መደበኛ ጨረታ ሰነድ ይዘትና አጠቃቀም፣ ስለ ጨረታ ግምገማ፣ ስለ ቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ጨረታ እና ሰለ አገልግሎት ግዥ በዝርዝር ገለጻ አድርገዋል፡፡   
በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ከየመ/ቤቱ የተውጣጡ ሰልጣኞች በቆይታቸው ሥልጠናው ጥሩ አቅም እንደፈጠረላቸውና የነበረባቸውንክፍተት ለመሙላትና ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት በየመ/ቤታቸው ወደ ተግባር ለመለወጥአጋዥ እንደሚሆንላቸውም ገልጸዋል፡፡
ለአምስት ቀናት በቆየው የመንግሥት ግዥ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ላይ ከ250 በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት