The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

በሀገራዊ ፖሊሲ ሰነዶች ላይ ስልጠና ተሰጠ

በሀገራዊ ፖሊሲ ሰነዶች ላይ ስልጠና ተሰጠ

የፌደራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና ሀገራዊ ህዳሴ፣በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግልና ፈተናዎቹ፣ በህገ መንግስታዊ መርሆዎችና ሴኩላሪዝም፣የልማታዊ ሲቪል ሰርቪስ የመገንባት ፋይዳና የሲቪል ሰርቪሱ ሚና፣እና የተሀድሶው መስመር በኢትዮጵያ በሚሉት ሰነዶች ላይ ከጥቅምት 11 ህዳር 4 ቀን 2007 ዓ.ም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እና ከተጠሪ መ/ቤቶቹ ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
አሰልጣኞቹ የኢትዮጵያን ጥንታዊና ዘመናዊ ታሪክን በአጭሩ፣ የኒዮ ሊበራሊዝምን አማራጭ በኣፍሪካና በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደትና በመመዝገብ ላይ ያሉ መሰረታዊ ለውጦች፣ ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ የተሃድሶ መስመሩና የአገራዊ ህዳሴ ጉዟችን ምዕራፍ፣ የልማታዊ ሲቪል ሰርቪስ ምንነትና አስፈላጊነት እና ሌሎች ርዕሶች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል፡፡The MoFED Training
ሰልጣኞችም በበኩላቸው ስልጠናው ሀገራዊ ፖሊሲውንና አቅጣጫውን ለማወቅና ለመገንዘብ ጥሩ አቅም እንደፈጠረላቸውና በየመ/ቤታቸው ወደ ተግባር ለመለወጥና የመንግስትን ሀገራዊ ፖሊሲ  አቅጣጫ በአግባቡ ተረድተው ወደ ስራ ለመሰማራት በእጅጉ እንደሚረዳቸውና እንደሚጠቅማቸው   ገልፀዋል፡፡

በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ  በተሳታፊዎች የቡድን ሥራ የተሠራ ሲሆን፣ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች እንዲሁም በአፈጻጸም ላይ ስለአጋጠሟቸው ችግሮች ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ለ20 ቀናት በቆየው የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እና የተጠሪ መ/ቤቶች የሀገራዊ ፖሊሲ ስልጠና ላይ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ እና፣መካከለኛ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት