The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ኤጀንሲው የተቆጣጣሪነት ሚና ላላቸው ፌዴራል ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር የተቆጣጣሪነት ሚና ላላቸው ለስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣ ለዳኞች እና ለጠቅላይ አቃቢ ህግ እንድሁም ከተመረጡ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ከነሐሴ 09 አስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ኩሪፍቱ ሪዞርትና ሆቴል መሰብሰቢያ አደራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ወ/ሮ መቅደስ ብርሃኑ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት በመክፈቻው ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ዋና ዓላማ የመንግስት ፋይናንስ ዘርፍ የሆነውን የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም የግዥ ሂደት ተግባራት አግባብ ባለው መልኩ ማስኬድ እንዲቻል የተቆጣጣሪነት ሚና ላላቸው ባለድርሻ አካላት በተቆጣጣሪነት ሙያ ላይ ለተሰማሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት በግዥ ላይ የሚውለው ከፍተኛ የሀገሪቷ ሀብት አግባብ ባለው መልኩ በስራ ላይ እንዲውል ለማስቻል ሀገራዊ ሀላፊነታችንን በተገቢው መልኩ ለመወጣት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተውጣጡ አሰልጣኞች በመንግስት ግዥ አላማና መርሆዎች፣ የመንግስት ግዥ የሚመራባቸው ሰነዶች፣ የግዥ ዕቅድና የግዥ ዑደት፣ በመንግስት ግዥ የሚታዩ ክፍተቶች፣ በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ዙሪያ የሚታዩ ስነ-ምግባር ጉድለት እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ጥሩ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የተቆጣጣሪነት ሚና ካላቸው የፌዴራል ተቋማት ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኤጀንሲው አሰልጣኞችና አመራሮች መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡በአዳማ ከተማ ኩሪፍቱ ሪዞርትና ሆቴል ለሶስት ቀናት በቆየው በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ላይ በርካታ የተቆጣጣሪነት ሚና ያላቸው የፌዴራል ተቋማት ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ከኤጀንሲው ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት