The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

ከኢትየጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ከፌዴራልና ከክልሎች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከኢትየጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ከፌዴራል እና ከክልል የከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ተቆጣጣሪ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡ክብርት ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በምክክር መድረኩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት መንግስት የተለያዩ የልማት ዕቅዶችን ነድፎ ተግባራዊ ለማድረግ መላውን የአገራችንን ህዝቦች በማሰተባበር ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በርካታ የልማት ሥራዎች ሲያከናውን መቆየቱንና ከዚህም የተነሳ በአገራችን በየዓመቱ ከሌሎች ተመሳሳይ ደረጃ ከሚገኙት የአፍሪካ ታዳጊ አገራት ጋር ሲነጻጸር በተሻለ መልኩ የኢኮኖሚ ዕድገት እየተመዘገበ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ዋና ዳይሬክተሯ ይህ የጋራ የውይይት መድረክ ምክከር እንዲያደርግባቸው የተዘጋጁት አጀንዳዎች እስካሁን በንግዱ ማህበረሰብ በኩል የተነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ በስራ ላይ ያለውን የመንግስት የግዥ ሥርዓት የሚዳስሱ እና የአፈጸጸም ግንዛቤ የሚያሳድጉ መሆኑ እነደሚታመንና ይህ የውይይት መድረክ የመንግሥትን የግዥ ስርዓት እና አሰራሩን ማንኛውንም ወገን በግልጽ መረዳት እነዲችልና አድሎአዊ አሰራርን በመከላከል የልማታችን ፀር የሆነውን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል ከፍተኛ አሰተዋፅኦ ያለው ከመሆኑም በላይ ለመንግስት ልዩ ልዩ ግዥዎች የተመደበ የህዝብ ገንዘብ ለታለመለት ዓላማና ግብ እንዲውል ከፍተኛ አሰተወጽኦ ያድርጋል ብለው እንደሚያስቡ ገልጸዋል፡፡፡

አቶ ሃብታሙ መንገሻ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የሕግ አገልግሎት ባለሙያ እየተሻሻለ የሚገኘውን የመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር አዋጅ ያካተታቸውን ዋና ዋና ጉዳዮችና ያለበትን ደረጃ፣ አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ምክንያት፣ ከጨረታ ሽያጭ ጋር ተያይዞ በድረ-ገጽ መመዝገብን በተመለከተ፣ ስለ ፐርፎርማንስ ግዥ፣ ስለ ላይፍ ታይም ኮስት አናሊስስ፣ የኮመን ዩዝርሰ አይተምን በተመለከተ፣ ስለ ልዩ አሰተያየት፣ ስለገበያ ጥናት ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ የመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር በ2010 በጀት ዓመት በመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ አገልግሎት ስለተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን በሚመለከት፣ ስለመድን ዋስትና፣ ቶነርና ጎማን በተመለከተ፣ ስለኬሚካል አወጋገድ ጉዳይ፣ ስለዓለም አቀፍ ግዥ፣ስለጥቅል ግዥ፣የአገር ውስጥ ምርትን በሚመለከት በዝርዝር አሰረድተዋል፡፡በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተለያዩ አሰተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ጥያቄዎችም ተነስተው ለጥያቄዎቹም መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ለአንድ ቀን በቆየው በዚህ የምክክር መድረክ ስብሰባ ላይ 150 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡


ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት