The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የፌዴራል መንግሥት የግዥና ንብረት አሰተዳደር ኤጀንሲ ከመላው ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከመላው የኤጀንሲው ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ጋር የ2010 የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2011 ዕቅድን በተመለከተ ሐምሌ 24 ቀን 2010 ዓ.ም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡ክብርት ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ– ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ኤጀንሲው በ2010 በጀት ዓመት በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ መሆኑንና በበጀት ዓመቱ የተከናወኑትን አበይት አፈጻጸሞችን ግምገማ አሰመልክተው ምን አቀድን? ምን ፈጸምን? ጥንካሬና ድክመታችንስ ምንድነው? ለ2011 በጀት  ዓመት የታቀደው ዕቅድ ምን ይመስላል? የሚለውን  ሃሳብ በማንሳት የብስሰባውን ዓላማ በማሳወቅ ከመላው የኤጀንሲው ሰራተኞች ጋር በጋራ መወያየት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ አድማሱ ማሞ የለውጥ ትግበራ ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የኤጀንሲውን የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀረቡ ሲሆን፣የተገልጋዮችን ቻርተርን በሚመለከት በአዲስ መልክ ተጠንቶና ተከልሶ ታትም ለተገልጋዮች እየተሰራጨ መሆኑን፣የኤጀንሲውን አገልግሎት አሰጣጥን በሚመለከት በተገልጋዮች የአስተያየት መስጫ መዝገቦች እና ሳጥኖችን በመጠቀም 30 ተገልጋዮች አስተያየታቸውን በፅሁፍ የሰጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 27ቱ ተገልጋዮች በተሰጣቸው አገልግሎት የረኩ መሆናቸውን ሲገልጹ፣ 3ቱ ተገልጋዮች በተሰጣቸው አገልግሎት ዕርካታ ያላገኙና መስተካከል ያለባቸውን በመጥቀስ አስተያየት መሰጠቱን አስረድተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በመንግሥት ግዥ አፈፃፀም ላይ 2274 የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶችና የክልል መ/ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች  መስልጠናቸውን፣ በመንግሥት ንብረት አስተዳደር ላይ 919 የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶችና የክልል መ/ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች  መሰልጠናቸውን፣ በመንግስት ግዥ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍና የተለያዩ መረጃዎች ለጠየቁ 1997 ተገልጋዮች መሰጠታቸውን፣ በመንግሥት ንብረት አስተዳደር ዙሪያ ከተለያዩ መ/ቤቶች ለቀረቡ 90 ጥያቄዎች  ሙያ ድጋፍ መሰጠቱን፣ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያን በሚመለከት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘዴዎች በመጠቀም በመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ዙሪያ በርካታ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆናቸውን፣የህትመት ሜዲያን በሚመለከት የኤጀንሲውን የሥራ እንቅስቃሴን የሚያሳይ

በቁጥር 2000 መፅሔት በማሳተም ለተገልጋይና ለባለድርሻ አካላት መሰራጨቱን፣በየወቅቱ የተከናወኑ ስብሰባዎችና ሥልጠናዎች  ዙሪያ  ማህበረሰብ ግንዛቤ እንዲኖረው የሚረዱ በርካታ ዜናዎች ተሰርተው በኤጀንሲው ድረ-ገጽ  ለተገልጋዮች ተደራሽ መሆናቸውን፣የታገዱ አቅራቢዎችን ስም ዝርዝር በድረ-ገጽ መጫኑን፣ የኤጀንሲው ድረ-ገፅ የዌብ ቤዝድ አፕሊኬሽን የማሻሻል ስራ መከናወኑን፣ በመቀጠልም ዳይሬክተሩ ኤጀንሲው ለሚያከናውናቸው ፕሮገራሞች አፈጻፀሙ 83% መሆኑን፣ የ2009 ዓመታዊ የንብረት፣ የነዳጅ፣ የሰው ሀብት ቅጥር፣ የነዳጅ አጠቃቀምና የተሸከርካሪ ሠነዶች ላይ ምርመራ ተከናውኖ መላኩን፣ የ2ዐ10 በጀት ዓመት የ3ኛው ሩብ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ ኦዲት በምርመራ ላይ መሆኑን፣አዲሱ የአዋጅ ማሻሻያ በረቂቅ ደረጃ የተጠናቀቀ ቢሆንም የመንግስት የልማት ደርጅቶች በአዋጁ ውስጥ ማካታት ጋር ተያይዞ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማካሄድ አስተያየቶችን የመሰብሰብ ሥራ መከናወኑን፣ አስተዳደር መመሪያዎች ከአዋጁ መፅደቅ በኃላ የሚሠሩ ሲሆን የተወሰኑ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ረቂቅ መዘጋጀቱን፣ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ጥገና መመሪያ በረቂቅ ደረጃ ተዘጋጅቶ ለ10 መ/ቤቶች መላኩን፣ ለመንግስት ንብረት ማስወገድ የሚውል ረቂቅ የጨረታ ሠነድ ተዘጋጀቶ በስራ ላይ እንዲውል መደረጉን፣ በ2010 በጀት ዓመት በ94 መ/ቤቶች ላይ የግዥ አፈፃፀምና የንብረት አስተዳደር ኦዲት መደረጉን፣ በ34 መ/ቤቶች ላይ የኦዲት ክትትል ስራ መከናወኑን፣ 250 አቅራቢዎች በባለጀት መ/ቤቶች ላይ የሚያቀርቧቸውን አቤቱታዎች ውስጥ 232 በማጣራት እና የውሳኔ ሀሳብ በማዘጋጀት ለቦርድ አቅርቦ ውሳኔ ማሰጠቱ፣ የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች በአቅራቢዎች ላይ ያቀረቧቸውን 514 ውስጥ 379ኙ የጥፋተኝነት ሪፖርቶች በማጣራት ውሳኔ መሰጠቱ፣ ከ eGP ፕሮጀክት ጋር  በተያያዘ መቋቋም ካለባቸው 2 ኮሚቴዎች ውስጥ  የ e-GP Steering Committee የማቋቋም ስራ መከናወኑን፣ በተዘጋጀው TOR መሰረት የ E-Procurement በተዘጋጀው መሰረት የ ፕሮጀክት ማናጀር ቅጥር ተፈፅሞ ውል የገቡ አማካሪ ሥራ መጀመሩን፤ 169 የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች የ2010 የግዥ ዕቅድ አቅርበው መጠናቀሩን፣137 የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች የ2009 የግዥ ሪፖርት አቅርበው ወደ መረጃ ቋት መግባቱን፣ 139የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶችና የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የነዳጅ ፣ መለዋወጫ እና ቅባት አጠቃቀም  ወራዊ ሪፖርት የላኩ በመሆኑ መረጃው በኮምፒተር መረጃ ቋት ውስጥ እንዲገባ መደጉን፤146 የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተሽከርካሪ ብዛት፣ አይነትና ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ሪፖርታቸውን ወቅቱን ጠብቀው እንዲያቀርቡ በማድረግ መረጃው የኮምፒውተር መረጃ ቋት ውስጥ መግባቱን፣ ባለቤት የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጦ  ኤጀንሲው ተረክቦ እንዲያስተዳድራቸው በሚመለከታው አካል ዉሳኔ የተሰጣባቸውን ማስተዳደር /እንዲወገዱ/ መደረጉን፣ 5,496 አቅራቢዎች በኤጀንሲው ድረ-ገጽ ተመዝግበዋል፣ የተመዘገቡ አቅራቢዎች ቁጥር በአጠቃላይ 22,614 መድረሱን፣ የኤጀንሲው ወቅታዊ የአፈፃፀም ሪፖርቶች ተዘጋጅተው ከተገመገመ በኋላ ለገ/ኢ/ት/ሚ/ር፣ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት መላኩን፣ ክፍት የሥራ መደቦችን በቅጥር እና በደረጃ ዕድገት በ2010 ለማሟላት በተደረገው ጥረት 27 የሥራ መደቦች በቅጥር፣ 11 የሥራ መደቦች በደረጃ ዕድገት እንዲሁም 6 ሠራተኞች የኮንትራት ቅጥር በመፈፀም የሥራ መደቦች እንዲሟሉ መደረጉን፣ የኤጀንሲውን ሠራተኞች በተለያዩ የስልጠና አይነቶች አቅም የመገንባት ስራ መካሄዱን፣ በአዲሱ የአደረጃጀት መዋቅር ላይ ሠራተኞችን የመመደብና የማፅደቅ ስራ መሰራቱን፣ ማስረጃ ትክክለኛነት ለማጣራት ማስረጃዎቹ ወደ ተገኙበት የትምህርት ተቋማት በመፃፃፍ የማረጋገጥ ሥራ መሰራቱን፣ ሥርዓተ-ጾታን በሚመለከት የተለያዩ ሥልጠናዎች መሰጠቱን በዝርዝር ገልጸዋል፡፡

በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዉ በተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች መልስ እንዲሰጡበት ከተደረገ በኋላ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ማርታ እና የኤጀንሲው መ/ዋና ዳይሬክተር የማጠቃለያ ንግግር አድርገው የጋራ ግንዛቤ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡
ለአንድ ቀን በቆየሁ የዉይይት መድረክ ላይ 110 የሚሆኑ የኤጀንሲዉ ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡