The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለሶሰተኛ ዙር መሰጠት ጀመረ

የፌድራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2009 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመረውን የግዥና ንብረት አስተዳደር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለሶሰተኛ ዙር በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 28/2010 እስከ የካቲት 22/2010 ዓ.ም. እየሰጠ ይገኛል፡፡

የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 ዓ.ም. ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከሚያከናውናቸውም ዋና ዋና ተግባራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የግዥና የንብረት አስተዳደር ሥርዓቱ ወጥነት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ የሆነና ግልጽነት የተላበሰ የሙያ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመራ ማስቻል ነው፡፡ በመሆኑም ከ2 የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች፣ ከ9 ክልሎች፣ ከድሬደዋ ከተማ አሰተዳደር፣ ከ48 ዩኒቨርሲቲዎች እና ከ5 ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች  ለተውጣጡ የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎችበBasic level, Essential level and Advanced level በድምሩ ለ260 ሠልጣኞች በቂ ልምድ እና ከፍተኛ ብቃት ባላቸው ከኤጀንሰው፣ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ አሰልጣኞች ሥልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡ከፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ  በትብብር የሚሰጠው ስልጠና ሰለ ግዥ አዋጅ፣  መመሪያ፣ ማኑዋል፣ ስለጨረታ ሰነድ እንዲሁም ሰለ ዓለም ዓቀፍ ግዥ ምርጥ ተሞክሮ፣ ሰለ ግዥዘዴዎች፣ ሰለ ግዥ ዕቅድ፣ ሰለ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና እርምጃዎች፣ስለንብረት አያያዝና አጠቃቀም ሰፋ ያለ ስልጠና  ይሰጣል፡፡ በመጨረሻም የመመዘኛ ፈተና በመስጠት ሶስቱም የሥልጠና ደረጃ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚጠናቀቅ ገለጻ ተደርጓል፡፡ይህ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ቀጣይነት ያለው ሲሆን፣ በዘርፉ የሚታዩትንም የአቅም ክፍተቶች በዘላቂነት ባለው መልኩ ይፈታል ተብሎ ይታመናል፡፡

በመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት