The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የግዥና ንብረት አስተዳደር የሙያ ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለሁለተኛ ዙር ተሰጠ

የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2009 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመረውን የግዥና ንብረት አስተዳደር  የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለሁለተኛ ዙር በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 27/2010 እስከ ህዳር 23/2010 ዓ.ም. ሰጠ፡፡

የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 ዓ.ም. ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከሚያከናውናቸውም ዋና ዋና ተግባራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የግዥና የንብረት አስተዳደር ሥርዓቱ ወጥነት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ የሆነና ግልጽነት የተላበሰ የሙያ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመራ ማስቻል ነው፡፡በመሆኑም 100 ከሚሆኑ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች በBasic level, Essential level & Advanced level በድምሩለ150 ሠልጣኞች ሥልጠናው ተሰጥቷል፡፡ከፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ  በትብብር የተሰጠው ስልጠና ሰለ ግዥ አዋጅ፣  መመሪያ፣ ማኑዋል፣ስለጨረታ ሰነድ እንዲሁም ሰለ  ዓለም ዓቀፍ ግዥ ምርጥ ተሞክሮ፣ ሰለ ግዥ ዘዴዎች፣ ሰለ ግዥ ዕቅድ፣ ሰለ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና እርምጃዎች፣ ስለንብረት አያያዝና አጠቃቀም ሰፋ ያለ ስልጠና  ተሰጥቷል፡፡ሰልጣኞችም በቡድን ስራ የተሳተፉ ሲሆን፣ በመጨረሻም የመመዘኛ ፈተና በመስጠት ሶስቱም ደረጃ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሥልጠናው ተጠናቋል፡፡ይህ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ቀጣይነት ያለው ሲሆን፣ በዘርፉ የሚታዩትንም የአቅም ክፍተቶች ዘላቂነት ባለው መልኩ ይፈታል ተብሎ ይታመናል፡፡

በመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት