Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

General

አብሮ መስራት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

(ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአሰራር ስርዓቱን በማዘመንና ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ከማድረግ ጀምሮ ያልተቋረጥ ስልጠና፣ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየተቋማቱ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቭርሲቲ ስልጠና ሊሰጥ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ከዩኒቭርሲቲው አመራር ጋር ውይይት አድርጓል።

ከውይይቱ በተጨማሪ በባለስልጣኑ አመራር የስልጠና እና የዲጂታል ላይብራሪ ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን ባለስልጣኑ የያዘውን የዲጂታል ግዥና ንብረት ስራ የሚያግዝ እና ለሰልጣኞችም ምቹ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

ርዕይ የሚሳካው በጸሎት ሳይሆን በስራ ነው። አቶ ዳንኤል ገረመው

(ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች የ2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጻምን በጋራ ገምግመዋል።

የሩብ ዓመቱን የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የተቋሙ ስራ አመራረ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ሲሆኑ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዘመናዊ የመንግስት ግዥና ንብረት ስርዓትን በማጠናከር በ2022 በአፍሪካ አርዓያ ከሆኑ የግዥና ንብረት ተቆጣጣሪ ተቋም የመሆን ርዕይን ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ርዕይው እውን የሚሆነው በጸሎት ሳይሆን በስራ መሆኑን አመላክተዋል።

ሪፖርቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥራትና ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ እየተገበራቸው ከሚገኙ የዲጂታል ስራዎች እጅግ ጎልተው ከታዩ ተግባራት ውስጥ ጥቂቶች መሆናቸውን ያመላከተ ሲሆን የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ አተገባበር፣ የተሽከርካሪ አስተዳደር፣ የኤሌክትሮኒክ ትምህርት፣ ኤሌክቶኒክ ደብዳቤ መለዋወጫ፣ ዲጂታል አስተያየት እና ቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓቶች ከተጠቀሱት ዲጂታል ስራዎች ጥቂቶች ናቸው።

በሌላ በኩል አዋጅ 1333/2016 ለባለስልጣኑ አዳዲስ ተግባርና ሀላፊነቶችን ይዞ የመጣ መሆኑን ተከትሎ መመሪያዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን የማዘጋጀትና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ የማድረስ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራቱ በሪፖርቱ የተካተተ ሲሆን ተቋሙን የሚመጥን የሪፎርም ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ተቋሙ እየተገበራቸው የሚገኙትን የዲጂታል ስራዎች እና የአሰራር ስርዓቶች ከተገልጋዩ ማህበረሰብ ጋር ለማላማድ ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎችና ድጋፎች እየተሰጡ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ሪፖርቱን ተከትሎ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በግዥና ንብረት ባለስልጣን  ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት በሩብ ዓመቱ ከፍተኛ ስራ መሰራቱን አንስተው በቀጣይ ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር፣ የአገልግሎት ጥራትን ማሳደግ እና የእውቀት ሽግግር ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

በመጨረሻም ስራዎችን ያለ ጉድለት መፈጸምን እና አገልጋዮች ሆኖ መገኘትን ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ባህሪው እንዲያደረገው በማሳሰብ ግምገማው ተጠናቋል።

Discussion were held with UNOPS Procurement Advisor

(October 13/2025), The Federal Government Procurement and Property Authority is an institution that is working diligently to strengthen a modern government procurement and Property system and become one of the leading institutions in Africa by 2028. The authority has been able to digitalize operations to realize this vision, and fulfill its assigned responsibilities with high efficiency and increase the quality of service.
In particular, it has been given extensive functions and responsibilities under Proclamation 1333/2024, and it has been prepared guidelines and operating systems to carry out these functions and responsibilities, including Standard Ben Documents and Life Cost Analysis Documents. Therefore, the institution held discussions with UNOPS Procurement Advisor James Landels to improve the quality of the Life Costing Analysis document it is currently preparing. During the discussion, the content of the Life Costing Guidance document and UNOPS’s life-cycle costing guidance, as well as the overall procurement policy, were reflected for further discussion. In the discussion, to enhance the quality of the LCA document being prepared by the PPA, procurement experiences from various countries were presented by James, and discussions were held on the preliminary preparations and documents that should be prepared to ensure sustainable procurement.

ባለስልጣኑ የሰንደቅአላማን ቀን በድምቀት አከበረ።

(ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም) የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የሰንደቅ አላማ ቀን ከእቅድና ፕላን ሚኒስቴር እንዲሁም ከመንግስት ግዥ አገልግሎት ጋር በመሆን በድምቅት አክብሯል።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን  ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ማንሰራራት አዲስ ዘምን ድል ብሥራት፣ የኅብረብሔራዊነታችን እና የአብሮነታችን የታሪክ ማብሰሪያ ዓርማ፣ ለኢትዮጵያ ሕዳሴ፣ የጀግንነታችንና የአያበገሬነታችን መገለጫ፣ የነፃነታችን ማማ፣ ለኢትዮጵያ ዐዲስ ዘመን ከፍታ፣ የዘመናት የነጻነታችንና የሥልጣኔያችን አብሪ ኮከብ፣ የሕዳሴያችን ሕያዊ ምስክር፣ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነታችን መገለጫ፤ የሀገራችን ታላቅነት ማብሰራያ፣ የብልፅግናችንና የሐገራዊ ከፍታችን ብርሃን ማሳያ፣ ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ፣ ኢትዮጵያ በልጆቿ ቆራጥ አመራር ፈተናዎችን አሸንፋ ትሻገራለች በሚሉ መልዕክቶች ደምቆ እየተከበረ ይገኛል።