Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ ከብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ፡፡

የመ/ግ/ን/ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ በንግግራቸዉ ለኢጂፒ ሲስተም ትስስር ትግበራ አጋዥ የሆነ የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም መድረኩ መዘጋጀቱን የገለጹ ሲሆን ትስስሩ በግዥዉ ዘርፍ ያሉ የአሰራር ጉድለቶችን ለማስወገድና ማነቆዎችን ጭምር ለመፍታት ብሎም ከብክነት በጸዳ መንገድ ለመተግበር ያስችላል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አያይዘዉም  ሲሰተሙን ከብሄራዊ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰሩ ያለዉን ፋይዳ ሲገልጹ ዕዉነተኛ ማንነትን በማረጋገጥ የሲስተሙን ተዓማኒነት ከፍ ማድረግ ቀዳሚዉ ነዉ ብለዋል፡፡

በመቀጠልም የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ መሆን በኤሌክትሮኒክ የመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ እንደቅድመ ሁኔታ እንደሚጠየቅ የገለጹ ሲሆን ይህን ተግባራዊ በማያደርጉ ላይ ሲስተሙ በራሱ ዝግጁ (Active) እንደማይሆን ጭምር ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ዮዳሄ ዓርኣያስላሴ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ስራ አስፈጻሚ የሲሰተሙን ጠቀሜታ በማስቀደም ስምምነቱን በታላቅ ደስታና ኩራት እንደተቀበሉትና ለተግባራዊነቱም የጋራ ብርቱ ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *