Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ ቀልጣፋ አገለግሎት መስጠት የሚያስችል ስርዓት እየገነባ መሆኑ ተገልጸ።

(ህዳር 17/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስርዓት እየገነባ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሯ ይህን የገለጹት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው።

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባለስልጣኑን የስራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ሲሆን ባለፉት አራር ወራት የተሰሩ አበይት ክንውኖችንም አዳምጧል።

ክብርት ወ/ሮ መሰረት በሪፖርታቸው ተቋሙ የአሰራር ስርዓቱን በማዘመን ጥራት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የዲጂታል ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን የገለጹ ሲሆን የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ፣ ዲጂታል የአስተያየት መስጫ፣ ዲጂታል የቅሬታ ማስተናገጃ፣ ዲጂታል የብልሹ አሰራርና የሙስና ጥቆማ መስጫ፣ ዲጂታል የኦዲት አገልግሎትና የነዳጅና ተሽከርካሪ ስምሪት በምሳሌንት ተነስተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሪፎርም የትግበራ ምዕራፍ ላይ መሆኑን አንስተው በዚህም የተቋማዊ ለውጥ ማኑዋል፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ የስርዓተ ጾታና ማህበራዊ ማካተቻ ማኑዋል እና ሌሎች ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የመንግስት ግዥን እና ንብረት አስተዳደርን ዘመናዊ በማድረግ የሀገር ሀብት ከብክነት ለመታደግና ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ዋጋ እንዲያስገኝ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል። በዚህ ረገድ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) ትልቅ ሚና እየተጫወት እንዳለና ስርዓቱም ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በሁሉም የፌዴራል ተቋማት ተግባራዊ መደረጉን አመላክተዋል።

ከገለጻው በኋላ ቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታውን ያካሄደ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥራትና ቅልጥፍናን የተቋሙ ባህል ለማድረግ እያከናወነው የሚገኘውን የዲጂታል ስራ የሚበረታታ መሆኑን በግበረ መልሳቸው አሳይተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *