ርዕይ የሚሳካው በጸሎት ሳይሆን በስራ ነው። አቶ ዳንኤል ገረመው

(ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች የ2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጻምን በጋራ ገምግመዋል።
የሩብ ዓመቱን የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የተቋሙ ስራ አመራረ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ሲሆኑ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዘመናዊ የመንግስት ግዥና ንብረት ስርዓትን በማጠናከር በ2022 በአፍሪካ አርዓያ ከሆኑ የግዥና ንብረት ተቆጣጣሪ ተቋም የመሆን ርዕይን ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ርዕይው እውን የሚሆነው በጸሎት ሳይሆን በስራ መሆኑን አመላክተዋል።
ሪፖርቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥራትና ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ እየተገበራቸው ከሚገኙ የዲጂታል ስራዎች እጅግ ጎልተው ከታዩ ተግባራት ውስጥ ጥቂቶች መሆናቸውን ያመላከተ ሲሆን የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ አተገባበር፣ የተሽከርካሪ አስተዳደር፣ የኤሌክትሮኒክ ትምህርት፣ ኤሌክቶኒክ ደብዳቤ መለዋወጫ፣ ዲጂታል አስተያየት እና ቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓቶች ከተጠቀሱት ዲጂታል ስራዎች ጥቂቶች ናቸው።
በሌላ በኩል አዋጅ 1333/2016 ለባለስልጣኑ አዳዲስ ተግባርና ሀላፊነቶችን ይዞ የመጣ መሆኑን ተከትሎ መመሪያዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን የማዘጋጀትና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ የማድረስ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራቱ በሪፖርቱ የተካተተ ሲሆን ተቋሙን የሚመጥን የሪፎርም ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ተቋሙ እየተገበራቸው የሚገኙትን የዲጂታል ስራዎች እና የአሰራር ስርዓቶች ከተገልጋዩ ማህበረሰብ ጋር ለማላማድ ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎችና ድጋፎች እየተሰጡ እንደሚገኙም ተገልጿል።
ሪፖርቱን ተከትሎ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት በሩብ ዓመቱ ከፍተኛ ስራ መሰራቱን አንስተው በቀጣይ ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር፣ የአገልግሎት ጥራትን ማሳደግ እና የእውቀት ሽግግር ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
በመጨረሻም ስራዎችን ያለ ጉድለት መፈጸምን እና አገልጋዮች ሆኖ መገኘትን ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ባህሪው እንዲያደረገው በማሳሰብ ግምገማው ተጠናቋል።









0 Comments